መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“አብዛኞቻችን የራሳችን ሃይማኖት አለን። ይሁንና አምላክ የፈለግነውን ሃይማኖት ብንመርጥ ግድ የማይሰጠው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ማቴዎስ 15:9ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ትምህርት እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተን እንድናውቅ የሚያስችሉንን ኢየሱስ የጠቀሳቸውን አራት መንገዶች ያብራራል።” በገጽ 16 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! የካቲት 2010
“አንዳንዶች በፈጣሪ ሲያምኑ ሌሎች ደግሞ እንዲህ ያለው እምነት ከሳይንሳዊው አስተሳሰብ እንደራቀና ምክንያታዊ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ በዚህ ረገድ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው እውነተኛ እምነት በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ነው። [ዕብራውያን 11:1ን አንብብ።] ይህ ርዕስ በፈጣሪ ላይ ለማመን የሚያስችሉ አንዳንድ ማስረጃዎችን ይጠቅሳል።” በገጽ 22 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“መጽሐፍ ቅዱስን የሚመለከቱት የአምላክ ቃል እንደሆነ አድርገው ነው ወይስ እንዲሁ ጥሩ መጽሐፍ እንደሆነ አድርገው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በዚህ ጉዳይ ላይ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነና እንዲህ ማድረጉ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! መጋቢት 2010
“እንደ ብዙዎች ሁሉ እርስዎም የተፈጥሮን ውበት እንደሚያደንቁ ተስፋ አደርጋለሁ። ተፈጥሮ ጥበብ የተንጸባረቀበት ንድፍ አለው ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም መዝሙር 104:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በተፈጥሮ ላይ የሚታየውን ንድፍ የሚያሳዩ አንዳንድ አስገራሚ ምሳሌዎችን የሚጠቅስ ሲሆን ከእነዚህ ነገሮች ምን ትምህርት እንደምናገኝም ይገልጻል።”