መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት
መጋቢት 22 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 10-13
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 10:17-27
ቁ. 2፦ የገና በዓል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው? (rs ገጽ 176 አን. 2 እስከ ገጽ 177 አን. 1)
ቁ. 3፦ የዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማው ለምንድን ነው?
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከት ማስታወቂያ ካለ ተናገር።
15 ደቂቃ፦ የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ ልዩ እትም ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። የዚህን እትም ይዘት ተናገር። መጽሔቱን ለማበርከት ምን ጥያቄ ለማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ለማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙትን ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እርዷቸው። በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን፣ የቀዘቀዙ አስፋፊዎችንና ሌሎችን በመርዳት ረገድ አስፋፊዎች ምን ድርሻ እንዳላቸው የሚገልጽ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። (የመጋቢት 2008 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።) አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚነበቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሁሉም እንዲያነቡ አሳስባቸው።