ሰኔ 28 የሚጀምር ሳምንት
ሰኔ 28 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
lv ምዕ. 15 አን. 10-17፤ በገጽ 177 የሚገኘው ሣጥን
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 3-6
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን ይዘት ከልስ። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሰ ትምህርቶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ተጠቅሞ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሌላ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ በማድረግ ክፍልህን ደምድም።—የነሐሴ 2007 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።
15 ደቂቃ፦ ከሕፃንነቱ ጀምሮ ሠልጥኗል። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ጢሞቴዎስ ቀናተኛና ውጤታማ ወንጌላዊ በመሆኑ ይታወቅ ነበር። (ፊልጵ. 2:20-22) እንዲህ ሊሆን የቻለበት አንዱ ምክንያት እናቱና አያቱ ከሕፃንነቱ ጀምሮ መንፈሳዊ ሥልጠና ስለሰጡት ነው። (2 ጢሞ. 1:5፤ 3:15) ወላጆች ልጆቻቸው ውጤታማ ወንጌላውያን እንዲሆኑ ማሠልጠን የሚችሉባቸው ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳቦች የሚከተሉት ናቸው። (1) ልጃችሁን ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አገልግሎት ይዛችሁት ውጡ፤ እንደ ዕድሜውና እንደ ችሎታው በአገልግሎት እንዲሳተፍ አሠልጥኑት። (ምሳሌ 22:6) (2) ለአገልግሎት ቅድሚያ በመስጠት ጥሩ አርዓያ ሁኑ። (ፊልጵ. 1:9, 10) (3) በቤተሰብ አምልኮ ወቅትም ሆነ በሌላ ጊዜ ለስብከቱ ሥራ ፍቅርና አድናቆት እንዲኖረው አድርጉ። (ዘዳ. 6:6, 7) (4) በአስተሳሰባችሁም ሆነ በአነጋገራችሁ ስለ አገልግሎት አዎንታዊ አመለካከት ይኑራችሁ። (ፊልጵ. 3:8፤ 4:8፤ 1 ጢሞ. 1:12) (5) በቤተሰብ መልክ በአገልግሎት አዘውትራችሁ በመካፈል ልማድ አድርጉት። (ሥራ 5:41, 42) (6) በአገልግሎት ቀናተኞች ከሆኑ ወንድሞች ጋር ተቀራረቡ። (ምሳሌ 13:20) አድማጮች አገልግሎት አስደሳችና ውጤታማ እንዲሆንላቸው ወላጆቻቸው ያበረከቱት አስተዋጽኦ ካለ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።