የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 28, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 3 እስከ ሰኔ 28, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ዳዊት በአበኔር ሞት ማዘኑ ለእኛ ምን ትምህርት ይሰጠናል? (2 ሳሙ. 3:31-34) [w05 5/15 ገጽ 17 አን. 5፤ w06 7/15 ገጽ 21 አን. 9-10]
2. ናታን የሠራው ስህተት ምን ነበር? ይሖዋ ከነቢይነት ያልሻረውስ ለምንድን ነው? (2 ሳሙ. 7:3) [rs ገጽ 135 አን. 6]
3. ሁለተኛ ሳሙኤል 7:14 ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? [it-1 ገጽ 273 አን. 3፤ it-2 ገጽ 818 አን. 2]
4. ዳዊት ለሜምፊቦስቴ ያደረገለት ነገር የፍቅራዊ ደግነት መግለጫ የሆነው እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (2 ሳሙ. 9:7 NW) [w02 5/15 ገጽ 19 አን. 5]
5. በንጉሥ ዳዊት እና የጌት ሰው በሆነው ኢታይ መካከል ከነበረው ግንኙነት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (2 ሳሙ. 15:19-22) [w09 5/15 ከገጽ 27-28]
6. ሲባ በሜምፊቦስቴ ላይ ያቀረበው ክስ ሐሰት እንደነበር ከቅዱሳን መጻሕፍት መረዳት የምንችለው እንዴት ነው? (2 ሳሙ. 16:1-4) [w02 2/15 ከገጽ 14-15 አን. 11፣ የግርጌ ማስታወሻ]
7. የ80 ዓመቱ ቤርዜሊ ዳዊት ከእሱ ጋር በቤተ መንግሥት አብሮት እንዲኖር ሲጠይቀው ከእሱ ይልቅ ከመዓምን እንዲወስደው ሐሳብ ያቀረበው ለምንድን ነው? (2 ሳሙ. 19:33-37) [w07 6/1 ገጽ 24 አን. 13]
8. ዳዊት ታላቅ ሰው ለመሆን የበቃው በይሖዋ ትሕትና ነው የምንለው ለምንድን ነው? (2 ሳሙ. 22:36 NW) [w07 11/1 ገጽ 5 አን. 1 ፤ w04 11/1 ገጽ 29]
9. አዶንያስ፣ ዳዊት ገና በሕይወት ሳለ ዙፋኑን ለመውረስ የሞከረው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 1:5) [w05 7/1 ገጽ 28 አን. 5]
10. ሰለሞን ጥበብና ማስተዋል ለማግኘት ያቀረበውን ልመና ይሖዋ የሰማው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 3:9) [w05 7/1 ገጽ 30 አን. 2]