መስከረም 20 የሚጀምር ሳምንት
መስከረም 20 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 19-22
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 20:1-11
ቁ. 2፦ ገሮች መሆን ያለብን ለምንድን ነው? (ማቴ. 5:5)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው ይሖዋን መፍራት ካለበት እንዴት ሊወደው ይችላል? (rs ገጽ 199 አን. 1-2)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ከልስ። ለተደረጉት መልካም ነገሮች አመስግን። በአገልግሎት ያገኟቸውን ግሩም ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ለአንድ ወይም ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች ጥቀስ፤ ከዚያም ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን ተናገር።
10 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ክፍል ለሚያቀርቡ ወንድሞች የተሰጠ መመሪያ።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ ልጆቻችሁ የምሥራቹ አስፋፊዎች እንዲሆኑ እርዷቸው። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ በሚገኘው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ያልተጠመቀ አስፋፊ ልጅ ላለው ምሳሌ የሚሆን አንድ ወላጅ ቃለ ምልልስ አድርግ። ልጁ እድገት እንዲያደርግና ለአስፋፊነት ብቁ እንዲሆን የረዳው እንዴት ነው?