ሰኔ 6 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 13 አን. 12-20 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 34-37 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 35:1-18 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ዛሬ በእስራኤል ምድር የሚታዩት ሁኔታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው?—rs ከገጽ 224 አን. 2 እስከ ገጽ 225 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ከሉቃስ 12:13-15, 21 ምን ልንማር እንችላለን? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በጥያቄዎች በመጠቀም ጥሩ አድርጎ ማስተማር—ክፍል 2 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 237 አንቀጽ 3 እስከ ገጽ 238 አንቀጽ 5 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን አከናውነናል? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ላደረገው እንቅስቃሴ ጉባኤውን አመስግን፤ እንዲሁም በዚያ ወቅት ምን እንደተከናወነ ጥቀስ። በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 52 እና ጸሎት