የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 26, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. ሰዎች በሚያቀርቡልን ምስጋና ‘ልንፈተን’ የምንችለው እንዴት ነው? (ምሳሌ 27:21) [w06 9/15 ገጽ 19 አን. 11]
2. ለአንድ ሰው ሙሉ በሙሉ እርካታ የማያስገኘው ምን ዓይነት “ደስታ” ነው? (መክ. 2:1) [g 4/06 ገጽ 6 አን. 1, 2]
3. አንዳንድ ሰዎች በመክብብ 3:1-9 ላይ የሚገኘው ሐሳብ በዕድል ማመንን የሚደግፍ ማስረጃ እንደሆነ የሚያምኑ ቢሆንም በመክብብ 9:11 ላይ ሰለሞን ያሰፈረው ሐሳብ በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመን እያንዳንዱ ነገር እንዳልተወሰነ በግልጽ የሚያሳየው እንዴት ነው? [w09 3/1 ገጽ 4 አን. 4]
4. “እጅግ ጻድቅ” መሆን ምን አደጋ አለው? (መክ. 7:16) [w10 10/15 ገጽ 9 አን. 8, 9]
5. ለማግባት የሚያስቡ ሰዎች የትዳር ጓደኛ የሚሆናቸውን ሰው በችኮላ መምረጥ እንደማይኖርባቸው ማሕልየ መሓልይ 2:7 የሚጠቁመው እንዴት ነው? [w06 11/15 ገጽ 19 አን. 1፤ w80-E 4/15 ገጽ 19 አን. 7]
6. የሱላማጢሷ ‘ከንፈሮች የማር ወለላ ማንጠባጠባቸው’ እንዲሁም ‘ከአንደበቷ ወተትና ማር መፍለቁ’ ምን ያሳያል? (ማሕ. 4:11) [w06 11/15 ገጽ 19 አን. 6]
7. “ድንቅ መካር፣” “ኀያል አምላክ” እና “የዘላለም አባት” የሚሉት የማዕረግ ስሞች ኢየሱስ ስላሉት ባሕርያትና በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለሚገዛበት መንገድ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረን የሚያደርጉት እንዴት ነው? (ኢሳ. 9:6) [w91 4/15 ገጽ 5 አን. 7]
8. በዛሬው ጊዜ ‘ከሃዲ በሆነው’ የእስራኤል ብሔር የተመሰለችው ማን ናት? እሷን ለማጥፋት የይሖዋ “በትር” ሆኖ የሚያገለግለውስ ማን ነው? (ኢሳ. 10:5, 6 NW) [ip-1 ገጽ 145 አን. 4, 5፤ ገጽ 153 አን. 20]
9. ኢሳይያስ ባቢሎንን አስመልክቶ “የሚቀመጥባት አይኖርም” የሚል ትንቢት መናገሩ አስገራሚ የሆነው ለምንድን ነው? የዚህ ትንቢት ፍጻሜ ምን ዓይነት ትምክህት እንዲኖረን ያደርጋል? (ኢሳ. 13:19, 20) [g 11/07 ገጽ 9 አን. 4, 5]
10. ኢየሱስ “የዳዊትን ቤት መክፈቻ” የተቀበለው መቼ ነበር? ምንስ ለማድረግ እየተጠቀመበት ነው? (ኢሳ. 22:22) [w09 1/15 ገጽ 31 አን. 2]