የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/12 ገጽ 4
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 1/12 ገጽ 4

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።

◼ በትላልቅና በትናንሽ ከተሞች የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ጽሑፎችን ማንበብ እንደሚፈልጉ ተስተውሏል። በመሆኑም በዋነኝነት የአማርኛ ቋንቋ በሚነገርባቸው አካባቢዎች ጭምር የሚገኙ አስፋፊዎች ሁኔታዎችን በንቃት እንዲከታተሉና አስፈላጊ ሲሆን በሌሎች ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎችን እንዲይዙ እናበረታታቸዋለን። ወይም ደግሞ በክልላችሁ የሚገኙ አብዛኞቹ ሰዎች ሁለት ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ከሆነ በሁለቱም ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎችን በመያዝ ራሳቸው እንዲመርጡ አድርጉ። በመሆኑም የአገልግሎት የበላይ ተመልካቾች በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ተስማሚ ጽሑፎችን ለምሳሌ በእንግሊዝኛ፣ በቻይንኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሲዳምኛ፣ በትግርኛና በወላይትኛ የተዘጋጁ ትራክቶችን እንድታዙ እንጠይቃችኋለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እና መጽሐፌ የተባሉት መጻሕፍትም ከላይ በተጠቀሱት ቋንቋዎች ይገኛሉ። በተጨማሪም አምላክን አምልክ (በኦሮምኛ) እና ለዘላለም መኖር (ትግርኛ)፤ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! (ኦሮምኛ፣ ሲዳምኛ፣ ትግርኛና ወላይትኛ)፤ ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ (ትግርኛና ወላይትኛ)፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው (ትግርኛና ወላይትኛ)፤ የአምላክ ወዳጅ (ሲዳምኛና ወላይትኛ)፤ የሙታን መናፍስት (ኦሮምኛ፣ ሲዳምኛ፣ ትግርኛና ወላይትኛ)፤ መለኮታዊው ስም (ትግርኛ)፤ ሥላሴ (ወላይትኛ) እንዲሁም እንደ አንድ አካል ሆነው የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ የይሖዋ ምሥክሮች (ትግርኛ) የተባሉት ጽሑፎች ይገኛሉ። የተለያዩ ዓይነት ጽሑፎችን መያዛችሁ በአገልግሎታችሁ ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆኑ ይረዳችኋል የሚል እምነት አለን።

◼ ከየካቲት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “እምነት የምትጥሉት በይሖዋ ላይ ነው?” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።

◼ አዲስ የደረሰን፦ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 2001-2010 በእንግሊዝኛ፤ በድምፅ የተቀዳው ለይሖዋ ዘምሩ የተባለው ሲዲ ቁ. 3 እና ቁ. 4።

◼ በድጋሚ የደረሰን፦ የዳንኤል ትንቢት በአማርኛ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ