የአቀራረብ ናሙና
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“በዛሬው ጊዜ አምላክ ሕዝቦቹን የሚመራው በድርጅት መልክ ይመስልዎታል ወይስ በግለሰብ ደረጃ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በጥንት ጊዜ አምላክ ስላደራጃቸው ሕዝቦች ይህ መጽሔት ምን እንደሚል ልብ ይበሉ።” የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16ን ካወጣህ በኋላ በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
የካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አርማጌዶን በብዙዎች ዘንድ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። አርማጌዶንን ለማስቀረት ሰዎች ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ያለ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ‘አርማጌዶን’ የሚለው ቃል የሚገኘው በራእይ 16:16 ላይ ነው። [ጥቅሱን ካነበብክ በኋላ የመጽሔቱን ሽፋን አሳየው።] ይህ መጽሔት ለእነዚህ ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።”
የካቲት ንቁ!
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ከሌሎች ጋር መገናኘት ያስደስታቸዋል። በዚህ መንገድ ከሰዎች ጋር መገናኘት አደጋ ያለው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በኢንተርኔት አጠቃቀማችን ረገድ ይበልጥ ጠንቃቆች እንድንሆን የሚረዱንን መመሪያዎች ይዟል። [ከገጽ 6-9 ላይ ከሚገኙት ጥያቄዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በአንዱ ላይ ውይይት አድርጉ።] ይህ መጽሔት ከኢንተርኔት አጠቃቀም ጋር የተያያዙትን አደጋዎች ለይተው እንዲያውቁና እነዚህን አደጋዎች ማስወገድ የሚችሉበትን መንገድ እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል።”