የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“የተለያየ እምነትና ዜግነት ያላቸው ሰዎች በየቀኑ ይጸልያሉ። አምላክ ሁሉንም ጸሎቶች የሚሰማና መልስ የሚሰጥ ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የመስከረም 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው የመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ ተወያዩ፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
የመጽሔቱን የፊት ገጽ አሳየውና እንዲህ በማለት ጠይቀው፦ “እርስዎ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ።] ይህ ጥቅስ እንደሚናገረው ‘ክፉው’ ወይም ዲያብሎስ ዓለምን እየገዛ ነው። ሆኖም ይህ አንዳንድ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ዲያብሎስ የመጣው ከየት ነው? የራሱ ሕልውና ያለው አካል ነው? አምላክ ዓለምን እንዲገዛ የሚፈቅድለትስ እስከ መቼ ነው? ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ምን ሐሳብ እንደሚሰጥ ይናገራል።”
ንቁ! መስከረም
“ዛሬ ብዙ ሰዎች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ያሉባቸው ችግሮች ያስጨንቋቸዋል። መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ይህን ያህል ከባድ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ምክሮችን ተግባራዊ በማድረግ ገንዘባቸውን በአግባቡ መጠቀም ችለዋል። [በገጽ 8 እና 9 ላይ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብ።] ይህ መጽሔት ዕዳቸውን ለመክፈል ለተቸገሩ ሰዎች የሚሆኑ ጠቃሚ ሐሳቦችን ይዟል።”