የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ብዙ ሰዎች አምላክ በሠሩት ሥራ እንደሚፈርድባቸው ይሰማቸዋል። እርስዎ፣ የፍርድ ቀን በጉጉት የሚጠበቅ ነገር እንደሆነ አድርገው ነው የሚያስቡት ወይስ የሚያስፈራ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ አንድ መጽሔት ላሳይዎት።” የመስከረም 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“በብዙ የዓለማችን ክፍሎች፣ ሴቶች መድልዎና ግፍ ይደርስባቸዋል። የሚያሳዝነው ሃይማኖትም ለዚህ ጉዳይ አስተዋጽኦ አድርጓል። እርስዎስ አምላክ በእርግጥ ለሴቶች የሚያስብላቸው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚናገር አንድ ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላሳይዎት። [ኤፌሶን 5:28, 29ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ ለሴቶች ስላለው አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ያሳያል።”
ንቁ! መስከረም
“በርካታ ሰዎች፣ ምድር ላይ ያለው ሕይወት በኑክሌር ጦርነት አሊያም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ይጠፋል ብለው ያስባሉ። እንዲህ ያሉት ስለ ዓለም መጨረሻ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች መሠረት ያላቸው ይመስልዎታል? ወይስ የሰዎች ምናባዊ ፈጠራ ብቻ ናቸው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጽናና ተስፋ ይሰጣል። [መዝሙር 37:29ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ስለ ዓለም መጨረሻ የሚነገሩ አንዳንድ መላ ምቶችን የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን አሳማኝ ሐሳብ ያቀርባል።”