የካቲት 13 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 6 ከአን. 1-7 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢሳይያስ 52-57 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኢሳይያስ 56:1-12 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ጴጥሮስ የተወው የታማኝነት ምሳሌ እኛን የሚጠቅመን እንዴት ነው?—ዮሐ. 6:68, 69 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ማግባትን ይፈቅዳል?—rs ከገጽ 249 አን. 5 እስከ ገጽ 250 አን. 5 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የማስተማር ችሎታችሁን አዳብሩ።—ክፍል 1 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 56 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 57 አንቀጽ 2 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ የሚያሳድገው አምላክ ነው። (1 ቆሮ. 3:6) በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 55 አንቀጽ 1 እና 2 እንዲሁም ገጽ 138 አንቀጽ 3 እና 4 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “አገልግሎታችሁን ለማስፋት አሁኑኑ እቅድ አውጡ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ ጉባኤው በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት ለመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ምን ዝግጅት እንዳደረገ እንዲናገር የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹን ጋብዝ።
መዝሙር 16 እና ጸሎት