አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ሳንቲሞች
የመንግሥቱን ሥራዎች መደገፍ የምንችልበት አንዱ መንገድ ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው። ሆኖም የገንዘብ አቅማችን አነስተኛ ከሆነ ምን ማድረግ እንችላለን?
በአንድ ወቅት፣ ኢየሱስ አንዲት ድሃ መበለት በቤተ መቅደሱ የመዋጮ ዕቃዎች ውስጥ አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ሳንቲሞች ስትከት አየ። ይህች መበለት ለይሖዋ ያላት ፍቅር “በድሃ አቅሟ ያላትን ሁሉ፣ መተዳደሪያዋን በጠቅላላ” እንድትሰጥ አነሳስቷታል። (ማር. 12:41-44) ኢየሱስ ስለዚች ሴት ጠቅሶ መናገሩ ያደረገችው መዋጮ በአምላክ ፊት ትልቅ ዋጋ እንደነበረው ይጠቁማል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖችም የስብከቱን ሥራ በገንዘብ የመደገፍ ኃላፊነት ያለባቸው ሀብታም የሆኑት ክርስቲያኖች ብቻ እንደሆኑ አልተሰማቸውም። ሐዋርያው ጳውሎስ በመቄዶንያ የነበሩ ክርስቲያኖች በዚህ ረገድ የተዉትን ምሳሌ ጠቅሷል፤ እነዚህ ክርስቲያኖች “ከባድ ድህነት ውስጥ” የነበሩ ቢሆንም ‘የልግስና ስጦታ የመስጠት መብት እንዲሰጣቸው ይለምኑ እንዲያውም ይማጸኑ እንደነበር’ ተናግሯል።—2 ቆሮ. 8:1-4
በመሆኑም የምናደርገው መዋጮ ‘አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ሳንቲሞች’ ያህል ትንሽ ቢሆንም እነዚህ አነስተኛ መዋጮዎች ተዳምረው ብዙ ገንዘብ እንደሚያስገኙ መርሳት የለብንም። “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ” ከልብ ተነሳስተን መስጠታችን ለጋስ የሆነውን የሰማዩን አባታችንን ያስደስተዋል።—2 ቆሮ. 9:7