ሚያዝያ 30 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 9 ከአን. 1-8 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 32-34 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በግንቦት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ሃይማኖትን በተመለከተ ለሚነሱ የተቃውሞ ሐሳቦች መልስ መስጠት የሚቻልበት መንገድ። በማመራመር መጽሐፍ ከገጽ 329 አንቀጽ 3 እስከ ገጽ 332 አንቀጽ 3 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። በቀረቡት ሐሳቦች ላይ የተመሠረቱ አንድ ወይም ሁለት አጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። የሐዋርያት ሥራ 4:1-13, 18-20 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ እንዴት እንደሚረዳን ተወያዩበት።
5 ደቂቃ፦ “አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ሳንቲሞች።” በንግግር የሚቀርብ።
መዝሙር 13 እና ጸሎት