የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 30, 2012 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት ቀን የተገለጸው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. የኤርምያስ መጽሐፍ ለእኛ ጠቃሚ ነው የምንለው ለምንድን ነው? [መጋ. 5, bsi07-AM ገጽ 4 አን. 36]
2. በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ከስደት የሚያድነን እንዴት ነው? (ኤር. 1:8) [መጋ. 5, w05 12/15 ገጽ 24 አን. 18]
3. ቅቡዓን ክርስቲያኖች ወደ ‘ጥንቷ መንገድ’ የተመለሱት መቼና እንዴት ነው? (ኤር. 6:16) [መጋ. 12, w05 11/1 ገጽ 24 አን. 12]
4. በዛሬው ጊዜ “በጊልያድ የበለሳን ቅባት” አለ ማለት የምንችለው ለምንድን ነው? (ኤር. 8:22 NW) [መጋ. 19, w10 6/1 ገጽ 22 አን. 3 እስከ ገጽ 23 አን. 4]
5. ይሖዋ፣ ፍርድ ካስተላለፈ በኋላ “እጸጸታለሁ” ሲል ምን ማለቱ ነው? (ኤር. 18:7, 8 የ1954 ትርጉም) [ሚያ. 2, w01 11/15 ገጽ 13 አን. 20፤ jr-E ገጽ 151 ሣጥን]
6. ይሖዋ ኤርምያስን ያታለለው በምን መንገድ ነው? ከዚህስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ኤር. 20:7) [ሚያ. 2, w07 3/15 ገጽ 9 አን. 6፤ jr-E ገጽ 36 አን. 8]
7. በኤርምያስ 22:30 ላይ የሚገኘው አዋጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊትን ዙፋን የመውረስ መብት እንዳይኖረው ያደርጋል? [ሚያ. 9, w07 3/15 ገጽ 10 አን. 9]
8. ይሖዋ በጥንት ጊዜም ሆነ አሁን ያሉትን ሕዝቦቹን “በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ” ማለት የሚችለው ለምንድን ነው? (ኤር. 31:3) [ሚያ. 23, w04 4/15 ገጽ 14 አን. 11፤ jr-E ገጽ 142-145 አን. 8-11]
9. የአምላክ ሕግ በልብ ላይ የሚጻፈው እንዴት ነው? (ኤር. 31:33) [ሚያ. 23, w07 3/15 ገጽ 11 አን. 2]
10. ለአንድ የግዢ ውል ሁለት ሰነዶች ማዘጋጀት ያስፈለገበት ዓላማ ምንድን ነው? (ኤር. 32:10-15) [ሚያ. 30, w07 3/15 ገጽ 11 አን. 3]