ጥቅምት 1 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 15 ከአን. 18-21 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 4-6 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዳንኤል 4:18-28 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች በመናፍስታዊ ድርጊቶች ከመካፈል መቆጠብ ያለባቸው ለምንድን ነው? (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አምላክ በድሮ ጊዜ በምድር ላይ ለነበሩት አገልጋዮቹ መመሪያዎችን ያስተላልፍ የነበረው እንዴት ነው?—rs ከገጽ 280 አን. 4 እስከ ገጽ 281 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ በመጀመሪያው ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሁሉም ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ከልስ። ለተደረጉት መልካም ነገሮች ጉባኤውን አመስግን። በአገልግሎት ያገኟቸውን ግሩም ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ለአንድ ወይም ለሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች ጥቀስ፤ ከዚያም ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን ተናገር።
10 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። በንቁ! መጽሔት የሽፋን ርዕስ ዙሪያም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 26 እና ጸሎት