የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/12 ገጽ 4
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 9/12 ገጽ 4

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መስከረም እና ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ኅዳር እና ታኅሣሥ፦ ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል! ወይም እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ በተባለው ብሮሹር ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚችል ልታሳዩት ትችላላችሁ።

◼ በ2013 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር ሚያዝያ 1 በሚጀምረው ሳምንት ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም ልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 1 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።

◼ ከጥር 15, 2013 እትም ጀምሮ፣ ቀለል ባለ ቋንቋ የሚዘጋጀው የመጠበቂያ ግንብ የጥናት እትም በፈረንሳይኛ ቋንቋም ተዘጋጅቶ ይወጣል።

◼ መጋዘናችን ውስጥ አዲስ የገቡ፦ አማርኛ፦ የይሖዋ ምሥክሮች በኢትዮጵያ—ነፃነት አፍቃሪዎች (በድጋሚ የታተመ፣ የኢትዮጵያን ቲኦክራሲያዊ ታሪክ የያዘ ብሮሹር)፤ እንግሊዝኛ፦ በሲዲ ለይሖዋ ዘምሩ—በድምፅ የተቀነባበረ፣ ዲስክ 5፤ ሲዳምኛ፦ አፕላይ ዩርሰልፍ ቱ ሪዲንግ ኤንድ ራይቲንግ እና ‘ደቀ መዛሙርት አድርጉ’ (የጥምቀት ጥያቄዎችን የያዘ ቡክሌት)፤ ሶማልኛ፦ ትራክት፦ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ