የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“የሰው ሕይወት በጣም አጭር ነው ቢባል እንደሚስማሙ እርግጠኛ ነኝ። በሽታ ጠፍቶ ሰዎች ረጅም ዘመን የሚኖሩበት ጊዜ ይመጣ ይሆን ብለው አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ አንድ መጽሔት ላሳይዎት።” የጥቅምት 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ የተጠቀሰውን ጥቅስ አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ
“ብዙ ሰዎች በዓለም ላይ ሙስና መስፋፋቱ ያሳስባቸዋል። ይህን ችግር መቅረፍ የሚቻልበት መንገድ ያለ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ በሙስና ምክንያት ጉዳት ለሚደርስባቸው ሰዎች ምን እንደሚያደርግ የሚያሳይ አንድ ጥቅስ ላንብብልዎት። [መዝሙር 72:12-14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሙስና በቅርቡ እንዴት እንደሚወገድ ይናገራል።”
ጥቅምት ንቁ!
“ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ ይፈልጋሉ። በዛሬው ጊዜ ከትምህርት ቤት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች የኑሮ ውጣ ውረዶችን ለመቋቋም ዝግጁ የሆኑ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ጥበብንና እውቀትን ስለማግኘት ምን እንደሚል አንድ ጥቅስ ላንብብልዎት። [መክብብ 7:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ልጆች በትምህርት ቤት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚረዱ አምስት ነጥቦችን ይዟል።”