የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/11 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
km 9/11 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ

“በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ፣ ሁላችንም በቤተሰብ ውስጥ ውጥረት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል። የቤተሰባችንን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የጥቅምት 1⁠ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በገጽ 16 እና 17 ላይ ካሉት ንዑስ ርዕሶች መካከል አንዱን መርጣችሁ ተወያዩበት። በተጨማሪም በንዑስ ርዕሱ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አንብቡ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ ከቀሪዎቹ ጥያቄዎች መካከል በአንዱ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

ጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ

የመጽሔቱን የፊት ገጽ አሳየውና እንዲህ በማለት ጠይቀው፦ “አምላክን በተመለከተ የተነገረዎት ነገር ውሸት እንደሆነ ቢያውቁ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ እውነቱን ከውሸት መለየት ስለሚቻልበት መንገድ የተናገረውን እስቲ ይመልከቱ። [ዮሐንስ 17:17⁠ን አንብብ።] እንግዲያው ስለ አምላክ እውነቱን ሊነግረን የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ይህ መጽሔት ሰዎች ስለ አምላክ የሚናገሯቸውን አምስት ውሸቶች ያጋልጣል።”

ጥቅምት ንቁ!

“በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦችን እያነጋገርን ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ የሚያጋጥማቸው ከሁሉ የበለጠው ተፈታታኝ ሁኔታ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ወላጆች መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ምክር ይመራሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በ⁠ኤፌሶን 4:31 ላይ የሚገኘው ጥበብ ያዘለ ሐሳብ ለልጆች ተግሣጽ በምንሰጥበት ጊዜ ሊረዳን ይችላል። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወላጆች ልጆቻቸውን ከሕፃንነታቸው አንስቶ ጉርምስና ዕድሜ ላይ እስኪደርሱ ድረስ ሲያሳድጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር እንዴት ሊረዳቸው እንደሚችል ይናገራል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ