የአቀራረብ ናሙናዎች
በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ዛሬ የመጣነው የሰው ልጆች ችግሮች መፍትሔ ስለሚያገኙበት አንድ መንገድ ልንነግርዎት ነው። የሰው ልጆች ዓመፅንና ግፍን ጨምሮ ሌሎች ከባድ ችግሮችን የማስወገድ አቅም ያላቸው ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ለምታነጋግረው ሰው አቡነ ዘበሰማያት ወይም የጌታ ጸሎት ተብሎ የሚጠራውን ጸሎት በመጥቀስ ኢየሱስ፣ ለተከታዮቹ ስለ አምላክ መንግሥት መምጣት እንዲጸልዩ እንዳስተማረ ግለጽለት። ከዚያም የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አሳየው፤ በጥያቄው ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“ኢየሱስ ለተከታዮቹ ባስተማረው ብዙዎች በሚያውቁት አንድ ጸሎት ላይ ከሰዎች ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነበር፤ በዚህ ጸሎት ላይ የሚገኘውን አንድ ሐሳብ ላንብብልዎት። [ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ኢየሱስ ሲያስተምር ይህን መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠቅስ የነበረውስ ለምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ ጥሩ ማብራሪያ ሰምተው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት የአምላክ መንግሥት ምን እንደሆነና ወደፊት በምድር ላይ ምን ግሩም በረከቶችን እንደሚያመጣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ያብራራል።”
ንቁ! ጥቅምት
“ሰዎች የዚህን ጥያቄ መልስ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እያሳየናቸው ነበር። [የመጽሔቱን ሽፋን አሳየው።] አንድ ሰው እውነተኛ ስኬት ለማግኘት የግድ ሀብታም መሆን አለበት ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ለቁሳዊ ነገሮች ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት እንዲኖረን ይረዳናል። [ሉቃስ 12:15ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማንኛውም ሰው እውነተኛ ስኬት ማግኘት እንደሚችል ይናገራል። ይህ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ ይናገራል።”