የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ከሰዎች ጋር ትኩረት በሚስብ አንድ ጥያቄ ላይ አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነው። [የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አሳየው።] ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም በጥያቄው ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“ብዙ ሰዎች የወደፊቱ ጊዜ ያሳስባቸዋል። እርስዎ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ሲያስቡ ምን ይሰማዎታል? የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ይጠብቃሉ? ወይስ የወደፊቱ ጊዜ ያስፈራዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ገጽ 7 ላይ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብለት።] ይህ መጽሔት፣ አምላክ ወደፊት እንደሚፈጸሙ የተናገራቸውን ነገሮች የሚጠቅስ ከመሆኑም ሌላ እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ የምንሆንበትን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት
“ውጥረትን መቋቋም ስለሚቻልበት መንገድ ከሰዎች ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነው። ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ከድሮው ጋር ሲያነጻጽሩት አሁን ይበልጥ ውጥረት ውስጥ የሚገኙ አይመስልዎትም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረጋቸው ውጥረትን ለመቋቋም እንደረዳቸው አስተውለዋል። ከእነዚህ ምክሮች አንዱን ላሳይዎት። [ማቴዎስ 6:34ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ምክሮች፣ ለውጥረት መንስኤ የሆኑትን አራት ነገሮች መቋቋም እንድንችል የሚረዱን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ማስታወሻ፦ ይህ መጽሔት በተለይ በንግዱ ዓለም የተሰማሩ ሰዎችን ትኩረት ሊስብ ይችላል።