የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ከሰዎች ጋር ትኩረት በሚስብ አንድ ጥያቄ ላይ አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነው። [የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ የመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ጥያቄ አሳየው።] ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም በጥያቄው ሥር ባለው ሐሳብ እና በአንቀጹ ላይ ካሉት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ሲጋራ ማጨስ በየዓመቱ 6 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት ይቀጥፋል። በሲጋራ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ የሚቻል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች አምላክ ስለ ሲጋራ ያለውን አመለካከት በመማራቸው ከሲጋራ ሱስ ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ችለዋል። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላሳይዎት፤ ይህ ጥቅስ አንዳንድ ሰዎች ሲጋራ ማጨሳቸው በሌሎች ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ ቆም ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። [አንደኛ1 ቆሮንቶስ 10:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንድ ሰው አምላክ ስለ ሲጋራ ያለውን አመለካክት ማወቁ ከዚህ ሱስ እንዲላቀቅ የሚያነሳሳው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ
“ማኅበራዊ ድረ ገጾች ሰዎች ብዙ ጓደኛ እንዳላቸው እንዲሰማቸው አድርገዋል። እውነተኛ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ባሕርይ ያለው ሰው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የእውነተኛ ጓደኛ መለያ ከሆኑት ባሕርያት መካከል አንዱ ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር ላሳይዎት። [ያዕቆብ 1:19ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጥሩ ጓደኛ ለመሆን የሚረዱ አራት ነጥቦችን ይጠቅሳል።”