የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 26, 2013 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. ንጉሥ ሄሮድስ የማይገባውን ውዳሴና ክብር ከሰዎች ስለ መቀበሉ ከሚናገረው ዘገባ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? (ሥራ 12:21-23) [ሐምሌ 1, w08 5/15 ገጽ 32 አን. 7]
2. ወጣት ክርስቲያኖች የጢሞቴዎስን ምሳሌ በመመርመርና አርዓያውን በመከተል ምን ጥቅም ማግኘት ይችላሉ? (ሥራ 16:1, 2) [ሐምሌ 8, w08 5/15 ገጽ 32 አን. 10]
3. አቂላና ጵርስቅላ፣ አጵሎስ በምኩራብ ውስጥ “በድፍረት” ሲናገር ከሰሙት በኋላ ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ የረዱት እንዴት ነው? (ሥራ 18:24-26) [ሐምሌ 15, w10 6/15 ገጽ 11 አን. 4]
4. የይሖዋ ምሥክሮች የመስበክ ነፃነታቸውን ለማስከበር ሲሉ በሚኖሩበት አገር የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን ለመጠቀም የሚያነሳሳቸው ምን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያት አላቸው? (ሥራ 25:10-12) [ሐምሌ 22, bt ገጽ 198 አን. 6]
5. ሐዋርያው ጳውሎስ በሮም ታስሮ እያለም እንኳ ለመመሥከር የሚያስችለውን መንገድ ይፈልግ የነበረው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ የሚኖሩ የይሖዋ አገልጋዮች የእሱን ምሳሌ የሚከተሉት እንዴት ነው? (ሥራ 28:17, 23, 30, 31) [ሐምሌ 29, bt ገጽ 215-217 አን. 19-23]
6. መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነትን ከተፈጥሮ ውጪ ወይም አስነዋሪ እንደሆነ አድርጎ የሚገልጸው ለምንድን ነው? (ሮም 1:26, 27) [ነሐሴ 5, g1/12 ገጽ 28 አን. 7]
7. በ33 ዓ.ም. ‘ክርስቶስ ኢየሱስ የከፈለው ቤዛ በቀደሙት ዘመናት የተፈጸሙትን ኃጢአቶች’ ሊሸፍን የቻለው እንዴት ነው? (ሮም 3:24, 25) [ነሐሴ 5, w08 6/15 ገጽ 29 አን. 6]
8. ይሖዋ፣ ያጋጠሙን ሁኔታዎች በጣም ግራ የሚያጋቡ ከመሆናቸው የተነሳ ምን ብለን መጸለይ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ ሊረዳን የሚችል ምን ዝግጅት አድርጎልናል? (ሮም 8:26, 27) [ነሐሴ 12, w08 6/15 ገጽ 30 አን. 10]
9. “የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል አዳብሩ” የሚለው ማሳሰቢያ ምን መልእክት ያስተላልፋል? (ሮም 12:13) [ነሐሴ 19, w09 10/15 ገጽ 5-6 አን. 12-13]
10. ሐዋርያው ጳውሎስ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት” በማለት የሰጠውን ምክር በሥራ ላይ ማዋል የምንችለው እንዴት ነው? (ሮም 13:14) [ነሐሴ 26, w05 1/1 ገጽ 11-12 አን. 20-22]