በመጀመሪያው ቅዳሜ ጥናት ማስጀመር ላይ ትኩረት አድርጉ
ከግንቦት 2011 ጀምሮ አስፋፊዎች በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ ላይ ጥናት ለማስጀመር ጥረት እንዲያደርጉ ሲበረታቱ ቆይተዋል። በዚህ ረገድ እንዲረዳን፣ ለሕዝብ በሚሰራጨው የመጠበቂያ ግንብ እትም ላይ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” የተባለ ቋሚ ዓምድ ተዘጋጅቶልናል። በመሆኑም በመጀመሪያው ቅዳሜ የሚደረገው የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ የሚቀርበው ሐሳብ ይህን ዓምድ ተጠቅሞ እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሊሆን ይገባዋል፤ በተጨማሪም በዚህ ላይ የተመሠረተ ሠርቶ ማሳያ መቅረብ ይኖርበታል።
ሽማግሌዎች በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ ላይ ሁሉም ቡድኖች የስምሪት ስብሰባውን ለየብቻቸው እንዲያደርጉ አሊያም ጉባኤው በሙሉ ምናልባትም በመንግሥት አዳራሽ የስምሪት ስብሰባውን እንዲያደርግ ይወስኑ ይሆናል። ይሁንና ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የመንግሥት አዳራሹን የሚጠቀሙ ከሆነ የጉባኤው አባላት አንድ ላይ ስምሪት እንዲያደርጉ ሲባል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር የምንጠቀምበት ይህ ልዩ ቀን ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዞር ማድረግ አይገባም።