መስከረም 2 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 11 ከአን. 1-7 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ቆሮንቶስ 1-9 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ቆሮንቶስ 4:18 እስከ 5:13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ሰዎችና ቦታዎች እንደምናውቅ ሆኖ የሚሰማን መሆኑ ሪኢንካርኔሽን እውነት መሆኑን ያረጋግጣል?—rs ገጽ 316 አን. 2 እስከ ገጽ 318 አን. 1 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ሕመም ቢኖርባቸውም ደስተኛ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው?—ፊልጵ. 4:6, 7 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። በውይይት የሚቀርብ። መጽሔቶቹ በክልላችሁ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉበትን ምክንያት ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ባለው ጊዜ ውስጥ ተናገር። ከዚያም በመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሽፋን ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። በመቀጠልም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ እንዳሰቡ ጠይቅ። በንቁ! መጽሔቱ ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?” በሚለው ዓምድ ዙሪያም በተመሳሳይ መንገድ ጥያቄዎችን አቅርብ፤ ጊዜ ካለህ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔት አንድ ተጨማሪ ርዕስ ማከል ትችላለህ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ የበርናባስን ምሳሌ ተከተሉ። በውይይት የሚቀርብ። የበርናባስን ምሳሌ መከተል የወንጌላዊነት ሥራችንን ስናከናውን የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 32 እና ጸሎት