ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ነሐሴ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች፣ አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር፣ ማንበብ ለማይችሉ ወይም የማንበብ ችሎታቸው ውስን ለሆነ ሰዎች መጠቀም ይቻላል።) መስከረምና ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ኅዳር፦ የመንግሥት ዜና ቁ. 38.
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር ‘ለሁሉም ብሔራት፣ ነገዶችና ቋንቋዎች የሚሆን ምሥራች’ የሚል ርዕስ ያለው ይሆናል።
◼ በአዲስ አበባ ፒያሳ ጉባኤ ሥር የምልክት ቋንቋ ቡድን ተቋቁሟል። ይህ ቡድን ስብሰባዎችን በምልክት ቋንቋ የሚያደርግ ሲሆን በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ለሚኖሩ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚደረገውን የምሥክርነት ሥራም በበላይነት ይከታተላል። በመሆኑም በክልላችሁ ውስጥ መስማት የተሳነው ሰው እንዳለ ካወቃችሁ ይህን መረጃ ለጉባኤያችሁ ጸሐፊ ንገሩት፤ እሱም መረጃውን ወደ አዲስ አበባ ፒያሳ ጉባኤ ያስተላልፈዋል። እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለውን ቅጽ ለዚህ ዓላማ ብትጠቀሙ ተመራጭ ነው።
◼ በአዲስ አበባ እንግሊዝኛ ጉባኤ ሥር የቻይንኛ ቡድን መቋቋሙን ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። በቻይንኛ ስብሰባ የሚደረገው እሁድ ከሰዓት በኋላ በ10 ሰዓት ነው። በመሆኑም በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ቻይንኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በተመለከተ ያላችሁን መረጃ ወደዚህ ቡድን ብታስተላልፉ ደስ ይለናል። በዚህ ረገድ የጉባኤያችሁ ጸሐፊ አስፈላጊውን እገዛ የሚያደርግላችሁ ሲሆን መረጃውን ለመላክ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለውን ቅጽ ብትጠቀሙ የተሻለ ይሆናል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው እንግሊዝኛ ወይም ሌላ የውጭ አገር ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን የሚመለከቱ መረጃዎችንም በተመሳሳይ መንገድ ወደ አዲስ አበባ እንግሊዝኛ ጉባኤ እንድታስተላልፉ እንጠይቃችኋለን።