የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“ጤና ይስጥልኝ። የመጣነው ትዳርን ደስተኛ ለማድረግ በሚረዱ ሐሳቦች ላይ አጠር ያለ ውይይት ለማድረግ ነው። በትዳር ውስጥ ደስታ እንዲጠፋ የሚያደርገው ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው ይላሉ?” [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የመስከረም 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ጥያቄ ሥር ባለው ሐሳብ ላይ እና በዚያ ውስጥ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ በአንዱ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ብዙ ሰዎች ‘አምላክ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ ያሳስባቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የሚገርመው መጽሐፍ ቅዱስ ሐዘንና ሥቃይ የማይኖርበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። [ራእይ 21:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መከራ የበዛበትን አምስት ዋና ዋና ምክንያቶች ያብራራል። በተጨማሪም አምላክ መከራን ለማስወገድ ያደረገውን ዝግጅት ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም
“አንዳንዶች ከፆታ ሥነ ምግባር ጋር በተያያዘ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ሐሳብ ጊዜ ያለፈበትና የማያፈናፍን እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚሰጠው መመሪያ ጋር ይስማማሉ። እርስዎ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የመጽሐፍ ቅዱስን መሥፈርቶች መከተል ምን ጥቅም እንዳለው የሚናገር አንድ ጥቅስ ባነብልዎት ደስ ይለኛል። [ኢሳይያስ 48:18ን አንብብ። ከዚያም በገጽ 4-5 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።] ይህ መጽሔት ከፆታ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ሦስት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። በተጨማሪም በዚህ ረገድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶችን መከተል ያለብን ለምን እንደሆን ያብራራል።”