የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g04 10/8 ገጽ 29
  • “ሃሎዊንን ማክበር አንፈልግም!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ሃሎዊንን ማክበር አንፈልግም!”
  • ንቁ!—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሃሎዊን አመጣጥ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ሃሎዊን—እውነታው ምንድን ነው?
    ንቁ!—2013
  • በትምህርት ቤት የጸና አቋም መያዝ ጥሩ ውጤት አስገኝቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ሃሎዊንን የማላከብረው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2004
g04 10/8 ገጽ 29

“ሃሎዊንን ማክበር አንፈልግም!”

ቤልጅየም የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

ከላይ ያለውን ውሳኔ ያስተላለፉት በቲነን፣ ቤልጅየም የሚገኝ ትምህርት ቤት የአንድ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። ተማሪዎቹ እንደዚህ ያለ ውሳኔ ላይ ሊደርሱ የቻሉት እንዴት ነው? በቤልጅየም የሃሎዊንን በዓል ማክበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረ ነገር ነው። እንዲያውም በዚህ ትምህርት ቤት በዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊከበር የታሰበው ጥቅምት 31, 2002 ነበር። ስለዚህ የበዓሉ ቀን ከመድረሱ በፊት መምህሯ ለሁሉም ልጆች ስለ ሃሎዊን ሪፖርት እንዲያዘጋጁ አዘዘቻቸው። አክላም “ስለ ሃሎዊን የፈለጋችሁትን ያህል አስቀያሚ ሪፖርት መጻፍ ትችላላችሁ” አለቻቸው።

በክፍሉ ውስጥ ከነበሩት ተማሪዎች አንዱ የ10 ዓመቱ ማቲያስ ነበር። ማቲያስ እንደ ሃሎዊን የመሰሉ ታዋቂ በዓሎች ስውር አደጋ እንዳላቸው በጥቅምት 8, 2001 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ላይ ማንበቡ ትዝ አለው። ሃሎዊን አምላክን የማያስደስቱ ነገሮችን እንደሚያካትትም ተገነዘበ። ስለዚህ ማቲያስ በንቁ! መጽሔቱ ውስጥ በሰፈሩት ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ ሪፖርት አቀረበ። የማቲያስ መምህር ሪፖርቱን በደንብ ካነበበችው በኋላ ሃሎዊን ብዙ ጊዜ እንደሚታሰበው ምንም ጉዳት የማያስከትል በዓል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ ደረሰች። ከዚያም ማቲያስ በዚህ ርዕስ ለክፍሉ ተማሪዎች ንግግር እንዲያቀርብ ጠየቀችው።

ማቲያስ ንግግሩን ማቅረብ ሲጀምር አንዳንዶቹ ተማሪዎች ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር። እየቀጠለ ሲሄድ ግን ሁሉም በተመስጦ ያዳምጡት ጀመር። ንግግሩን አቅርቦ ሲያበቃ መምህሯ አሁንም ሃሎዊንን ማክበር ይፈልጉ እንደሆነ ተማሪዎቹን ጠየቀቻቸው። የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ በአንድ ድምፅ “አንፈልግም!” በማለት መለሱ። አንዲት ተማሪ “የሚዘገንን [በዓል] ነው!” በማለት ተናገረች። ሌላ ልጅ ደግሞ “ሃሎዊን የሞቱ ሰዎችን ይህን ያህል እንደሚያቃልል አላውቅም ነበር” ብሏል።

ከዚህ ቀደም ዓይናፋር የነበረው ማቲያስም ተጽዕኖዎች ቢኖሩም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እምነቱን አጥብቆ መያዝ እንዳለበት ከዚህ ተሞክሮ ማበረታቻ አግኝቷል። ከዚህም በላይ የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ ከመምህሩም ሆነ አብረውት ከሚማሩት ልጆች ከፍተኛ አክብሮት አትርፏል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ