የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በሚያዝያ ወር ከፍተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን 7,886 ሰዎች ጥናት ተመርቶላቸው ነበር! የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ከአምላክ የተላከ ምሥራች! በተባለው ብሮሹር መጠቀማችሁን እንድትቀጥሉ እናበረታታችኋለን። በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 25,496 ነበር፤ ይህ አኃዝ ፍላጎት ያላቸውና መረዳት የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይጠቁማል። በተጨማሪም በሚያዝያ ወር 1,120 ረዳት አቅኚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የሚያስመሰግን ነው። የወረዳ የበላይ ተመልካቹ በሚጎበኝበት ወር ላይ 30 ሰዓት በማገልገል ረዳት አቅኚ መሆን የሚቻልበት አዲስ ዝግጅት መደረጉ የይሖዋን ፍላጎት ለማስቀደም ያለንን ቅንዓት ለማሳየት ተጨማሪ አጋጣሚ እንደሚሰጠን ምንም ጥርጥር የለውም።