ኅዳር 11 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ኅዳር 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 14 ከአን. 10-16 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕብራውያን 1-8 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዕብራውያን 4:1-16 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ “ከላይ የሆነው ጥበብ” እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—ያዕ. 3:17, 18 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የሚያስፈልገው ሌላውን ሰው መውደድ ብቻ ነው?—rs ገጽ 326 አን. 3 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት የምንችለው እንዴት ነው? በኅዳር 15, 2013 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 8-9 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ ስንሰብክ የሚሰማንን ፍርሃት ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው? በውይይት የሚቀርብ፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድማጮችን ጠይቅ፦ (1) በር ስናንኳኳ ፍርሃት ከተሰማን ጸሎት የሚረዳን እንዴት ነው? (2) ጥሩ ዝግጅት የሚሰማንን ፍርሃት ለመቀነስ የሚረዳን እንዴት ነው? (3) ከወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጋር ስናገለግል የሚሰማንን ፍርሃት ለመቀነስ ምን ሊረዳን ይችላል? (4) በአገልግሎት የምናደርገውን ተሳትፎ ማሳደጋችን የሚሰማንን ፍርሃት ለመቀነስ የሚረዳን እንዴት ነው? (5) የፍርሃት ስሜታችሁን ለማሸነፍ የረዳችሁ ምንድን ነው?
10 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ሆሴዕ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 37 እና ጸሎት