መዝሙር 25
የደቀ መዝሙርነት መለያ
በወረቀት የሚታተመው
1. ጠቃሚ ሕግ አምላክ ሰጥቶናል፤
ልንታዘዘው ይገባል።
ንጉሣዊ ሕግ የተባለው፣
የ’የሱስ ዓይነት ፍቅር ነው።
ጌታ ይህን ፍቅር አሳየን፣
ለኛ በመስጠት ሕይወቱን።
እንከተል ፈለጉን ሁላችን፣
እንዳይጠፋ መለያችን።
2. እውነተኛ ፍቅር አይወድቅም፤
ደካሞችንም አይረሳም።
የፍቅር ዕዳ ስላለብን፣
እናገልግል ወንድሞችን።
እንዲህ ዓይነት ልዩ መዋደድ፣
አይገኝም የትም ብንሄድ።
እጅግ ጠንካራ ነው ይህ ዝምድና፤
አንውጣ ከዚህ ጎዳና።
(በተጨማሪም ሮም 13:8ን፣ 1 ቆሮ. 13:8ን፣ ያዕ. 2:8ን እና 1 ዮሐ. 4:10, 11ን ተመልከት።)