የካቲት 10 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 18 ከአን. 19-23 እና ሣጥን (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 25-28 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 25:19-34 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከክርስቶስ ጋር ለመግዛት ከሞት የሚነሱት እንደ እሱ ይሆናሉ—rs ገጽ 335 አን. 1-5 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ርኩስ ነገሮች—ይሖዋ ለጣዖት አምልኮና ለዓመፅ ያለው አመለካከት—w07 6/15 ገጽ 26-30፤ w08 6/15 ገጽ 9 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ዮሐንስ 4:6-26 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር —ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን በማስታወሻ ላይ መመዝገብ።” በውይይት የሚቀርብ። “ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” በሚለው ርዕስ ሥር የሚገኙትን ነጥቦች በምትወያዩበት ጊዜ የቀረቡት ሐሳቦች ለምን ጠቃሚ እንደሆኑ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 44 እና ጸሎት