ማስታወቂያዎች
◼ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ወይም የሚከተሉት ትራክቶች፦ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ? (T-30)፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል? (T-31)፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው? (T-32)፣ ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው? (T-33)፣ መከራ የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል? (T-34)፣ የሞቱ ሰዎች እንደገና በሕይወት መኖር ይችላሉ? (T-35)፣ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (T-36)፣ በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? (T-37)፣ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? (kt)። ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! መስከረም፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ ለሰዎች ያበረከትናቸውንም ሆነ ቤታቸው ላልተገኙ ሰዎች ትተናቸው የሄድናቸውን ትራክቶች በሙሉ በወሩ መጨረሻ ላይ ሪፖርታችንን ስንመልስ “ብሮሹሮችና ትራክቶች” በሚለው ዓምድ ሥር ሪፖርት ማድረግ ይኖርብናል። አንድ ሰው ፍላጎት ካለውና ጽሑፎችን ሌላው ቀርቶ ትራክት እንኳ ከወሰደ ተመልሰን ሄደን በማነጋገር ፍላጎቱን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።
◼ ጥቅምት 19, 2015 ከሚጀምር ሳምንት አንስቶ በእምነታቸው ምሰሏቸው የተባለውን መጽሐፍ በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ እናጠናለን። ጉባኤዎች የዚህን መጽሐፍ ተጨማሪ ቅጂዎች የሚፈልጉ ከሆነ በሚቀጥለው የጽሑፍ ትእዛዛቸው ውስጥ ማካተት ይኖርባቸዋል። የመጽሐፉን ኤሌክትሮኒክ ቅጂ መጠቀም የሚፈልጉ የታተመውን መጽሐፍ ከመውሰድ ይልቅ መጽሐፉን ከjw.org ማውረድ ይችላሉ።