የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮች ያልተጠበቁ ከመሆናቸው አንጻር ኢየሱስ ጭንቀትን ተቋቁሞ ስለ መኖር የሰጠው ምክር ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ይመስልዎታል? [ማቴዎስ 6:25ን አንብብ፤ ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ከገንዘብ፣ ከቤተሰብ ሕይወትና በግል ሕይወታችን ከሚያጋጥሙን ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚሰማንን ጭንቀት ለመቋቋም ሊረዳን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሐምሌ
“በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ በሚያጋጥሟቸው የተለያዩ ችግሮች ተተብትበዋል ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ችግሮች ሲያጋጥሙን፣ ያለን አመለካከት ለውጥ እንደሚያመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [ምሳሌ 24:10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የሚያጋጥሙንን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለመቋቋም የሚረዱ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮችንና እንዲህ እያደረጉ ያሉ ሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ ይዟል።”