የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የይሖዋ ድርጅት የቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በከፊልም ሆነ በሙሉ ከ120 በሚበልጡ ቋንቋዎች እንዲዘጋጅ አድርጓል። ሁላችንም ይህን ውድ ሀብት በአማርኛ ቋንቋ በማግኘታችን እጅግ ተደስተናል። ይህም ይሖዋ “ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ” ካለው ዓላማ ጋር የሚስማማ ነው። ያገኘነውን ይህንን መሣሪያ ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን። ከዚህም ሌላ በዋናው መሥሪያ ቤት ተወካይ ጉብኝት ወቅት በ80 የተለያዩ ቦታዎች 12,121 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች የተገኙ መሆኑ በጣም አስደስቶናል።