መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድህነት ባስከተላቸው አስከፊ ችግሮች እየማቀቁ ነው። እነዚህን ሰዎች ለመርዳት ምን ማድረግ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም 1 ጴጥሮስ 2:21ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለድሆች አሳቢነት በማሳየት ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ እንዴት መኮረጅ እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት 2006
“የምናረጀው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ የምናረጅበትን ምክንያት በተመለከተ የሚሰጠው ማብራሪያ አምላክ የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንድንችል ዝግጅት ያደረገበትን መንገድ ያሳያል። [ኢሳይያስ 25:8ን አንብብ።] ይህ የንቁ! መጽሔት እትም የእርጅናን ሂደት በተመለከተ በአሁኑ ጊዜ ያሉትን አንዳንድ አመለካከቶች ይመረምራል።”
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው በዚህ ጥቅስ ላይ በሰፈሩት ሁኔታዎች ሥር ቢገኙ ደስተኛ እንደሚሆኑ ይሰማዎታል? [2 ጴጥሮስ 3:13ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የተባሉት ምን እንደሆኑ ያብራራል። ከዚህም በላይ አምላክ ለምድር ያለውን ዓላማ ዳር ሲያደርስ ሕይወት ምን ያህል የተለየ እንደሚሆን ይገልጻል።”
ንቁ! ግንቦት 2006
“አንዳንድ ሰዎች በዚህ ዓለም ስኬት ማግኘት የሚፈልግ ሰው ቁጡ መሆን አለበት የሚል እምነት አላቸው። በተቃራኒው ኢየሱስ ምን እንዳለ ይመልከቱ። [ማቴዎስ 5:5, 9ን አንብብ።] እርስዎ በዚህ ሐሳብ ይስማማሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ሰላማዊ መሆን የሚያስገኛቸውን ሦስት ጥቅሞች ይገልጻል።” በገጽ 28 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።