መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“ምሥጢራዊ የሆነውን የአውሬውን ምልክት በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን መግለጫ ያህል የሰዎችን ትኩረት የሳቡ ርዕሶች ብዙ አይደሉም። ስለዚህ ምልክት ሰምተው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ራእይ 13:16-18ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢራዊ የሆነውን የአውሬውን ምልክት ትርጉም ለመፍታት የሚያስችሉ ፍንጮች ይዟል። ይህ መጽሔት እነዚህን ፍንጮች ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2004
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ሕይወታቸው በጥድፊያ የተሞላ በመሆኑ እረፍት ማግኘት በጣም ያስፈልጋቸዋል። ምናልባት ከ3, 000 ዓመታት በፊት በተጻፈው በዚህ አባባል እርስዎም ሳይስማሙ አይቀሩም። [መክብብ 4:6ን ከ1954 ትርጉም አንብብ። ከዚያም መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! መጽሔት የእንቅልፍ ዕዳ ካለብን ማወቅ የሚቻልባቸውን መንገዶችና ችግሩን ለማሸነፍ የሚረዱ ዘዴዎችን ይናገራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“አንዳንድ ሰዎች አሳዛኝ ክስተቶችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙት ነገሮች ሁሉ በአምላክ ፈቃድ የሚፈጸሙ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ስለዚህ ጉዳይ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ብዙ ሰዎች ይህንን ጸሎት ያውቁታል። [ማቴ 6:10 ሁለተኛውን ሐረግ አንብብ።] አምላክ ለምድር ያለው ፈቃድ ምንድን ነው? ፈቃዱስ ሙሉ በሙሉ የሚፈጸመው መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ በዚህ መጽሔት ላይ ይገኛል።”
Awake! Apr. 22
“በጊዜያችን አንዳንድ ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ሲያስቡ ምንም ተስፋ አይታያቸውም። እርስዎስ አንዳንድ ጊዜ እንደዚያ ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ሮሜ 15:4ን አንብብ።] ብዙ ሰዎች ተስፋ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ተስፋ እንዲኖረን የሚያደርጉንን ሰባት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያቶች ከዚህ የንቁ! መጽሔት ቢያነቡ እንደሚደሰቱ እርግጠኞች ነን።”