መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“በአንድ ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስ ‘ከትእዛዛት ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ነው?’ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ምን ብሎ እንደመለሰ ይመልከቱ። [ማርቆስ 12:29, 30ን አንብብ።] ኢየሱስ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በዚህ መጽሔት ላይ ‘ለአምላክ ያለንን ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?’ የሚለው ርዕስ የዚህን ጥቅስ ትርጉም ያብራራል።”
ንቁ! መጋቢት 2004
“የአምላክ የግል ስም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲጻፍ ይህን ይመስላል። [ሽፋኑን አሳየው።] አንዳንድ ሰዎች ስሙን ፈጽሞ መጥራት የለብንም የሚል አመለካከት አላቸው። ሌሎች ደግሞ በስሙ በስፋት ይጠቀማሉ። ይህ የንቁ! እትም ይህን አወዛጋቢ ጉዳይ ይመረምራል። ከዚህም በተጨማሪ አምላክን በስሙ ማወቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” መዝሙር 83:18ን አንብብ።
Mar. 22
ሰዎች የሚያውቁት አንድ አሳዛኝ ክስተት ከጠቀስክ በኋላ “አምላክ እንደዚህ ያሉ ነገሮች እንዲደርሱ ለምን እንደሚፈቅድ አስበው ያውቃሉ?” ብለህ ጠይቅ። [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ያዕቆብ 1:13ን አንብብ።] “በተለይ ለወጣቶች ተብሎ የተዘጋጀው ይህ ርዕስ አፍቃሪው ፈጣሪያችን በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ ለማስወገድ እስካሁን ጣልቃ ያልገባው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”