ሐምሌ 6 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 80 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 21 ከአን. 1-7 እና በገጽ 166 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 7-8 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት 8:27-34 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ቆርኔሌዎስ—ጭብጥ፦ ይሖዋ አምላክ አያዳላም—w13 6/1 ገጽ 8 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጭንቀትን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?—nwt ገጽ 28 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “የጥንቱን ዘመን አስታውስ።”—ዘዳ. 32:7
10 ደቂቃ፦ በሐምሌ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ ሁለቱን የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም በመግቢያዎቹ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች አንድ በአንድ ተወያዩባቸው።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ በር ላይ እንደቆሙ ጥናት ማስጀመር” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን የሚያበረታታ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 67 እና ጸሎት