በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ በር ላይ እንደቆሙ ጥናት ማስጀመር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሰዎችን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የአምላክን ቃል ልናስተምራቸው ይገባል። (ማቴ. 28:19, 20) ለዚህ ዓላማ ሲባል የተዘጋጁልንን መሣሪያዎች የምንጠቀም ከሆነ ሁላችንም ውጤታማ በሆነ መንገድ እውነትን ማስተማር እንችላለን። ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለው ብሮሹር በዋነኝነት የተዘጋጀው እውነትን ለሌሎች ለማስተማር እንድንጠቀምበት ታስቦ ነው። እንዲያውም ይህን ብሮሹር በመጠቀም ከግለሰቡ ጋር በተገናኘንበት በመጀመሪያው ቀን እዚያው በሩ ላይ ቆመን ጥናት ልናስጀምረው እንችላለን።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የመምራት ፍላጎት እንዲያድርባችሁ ይሖዋን በጸሎት ጠይቁ። በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማግኘት እንድትችሉ እንዲሁም እውነትን በማስተማር ረገድ ውጤታማ እንድትሆኑ ይሖዋ እንዲረዳችሁ ለምኑት።—ፊልጵ. 2:13
በቤተሰብ አምልኮ ወይም በግል ጥናት ፕሮግራማችሁ ላይ የተወሰነ ጊዜ ወስዳችሁ የመግቢያ ሐሳቡን በደንብ ተለማመዱት። እንዲህ ማድረጋችሁ በእርግጠኝነት ስሜት እንድትናገሩና በር ላይ እንደቆማችሁ ጥናት ማስጀመር እንድትችሉ ይረዳችኋል።