ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ነህምያ 9-11
ታማኝ አገልጋዮች ቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶችን ይደግፋሉ
የአምላክ ሕዝቦች እውነተኛውን አምልኮ በተለያዩ መንገዶች በፈቃደኝነት ደግፈዋል
ሕዝቡ የዳስ በዓልን በትክክለኛ መንገድ ለማክበር ዝግጅት አደረገ እንዲሁም በዓሉን አከበረ
ሕዝቡ የአምላክ ቃል ሲነበብ ለመስማት በየቀኑ ይሰበሰቡ ነበር፤ ይህም ደስታ አስገኝቶላቸዋል
ሕዝቡ ኃጢአታቸውን ተናዘዙ፣ ጸለዩ እንዲሁም ይሖዋ እንዲባርካቸው ጠየቁ
ሕዝቡ ሁሉንም ቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶች መደገፋቸውን ለመቀጠል ተስማሙ
ቲኦክራሲያዊውን ዝግጅት ምንጊዜም መደገፍ ሲባል የሚከተሉትን ነገሮች ይጨምር ነበር፦
ከይሖዋ አገልጋዮች መካከል ብቻ ማግባት
የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረግ
ሰንበትን መጠበቅ
ለመሠዊያው የሚሆን እንጨት ማቅረብ
ከእርሻም ሆነ ከከብት በኩሩን ለይሖዋ መስጠት