ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 74-78
ይሖዋ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሱ
ይሖዋ ባከናወናቸው መልካም ሥራዎች ላይ ማሰላሰል በጣም አስፈላጊ ነው
ማሰላሰል ከአምላክ ቃል ላይ ያነበብነውን ነገር በሚገባ ለመረዳትና ለሚቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ ልባዊ አድናቆት እንዲኖረን ይረዳናል
ስለ ይሖዋ በጥሞና ማሰላሰል አስደናቂ ሥራዎቹንና የሰጠንን ተስፋ እንድናስታውስ ይረዳናል
ከይሖዋ ሥራዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ፍጥረት
ስለ ፍጥረት ይበልጥ ባወቅን መጠን ለይሖዋ ያለን አድናቆት ይጨምራል
በጉባኤ ውስጥ ያሉ የተሾሙ ወንዶች
ይሖዋ አመራር እንዲሰጡ ለሾማቸው ወንድሞች መገዛት ይኖርብናል
የማዳን ሥራዎች
ይሖዋ ባከናወናቸው የማዳን ሥራዎች ላይ ማሰላሰላችን አገልጋዮቹን ለመንከባከብ ባለው ፍላጎትና ችሎታ ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል