ከሐምሌ 25-31
መዝሙር 79-86
መዝሙር 138 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“በሕይወታችሁ ውስጥ ትልቁን ቦታ የምትሰጡት ለማን ነው?”፦ (10 ደቂቃ)
መዝ 83:1-5—ሊያሳስበን የሚገባው ዋነኛው ነገር የይሖዋ ስምና ሉዓላዊነቱ መሆን አለበት (w08 10/15 13 አን. 7-8)
መዝ 83:16—ከአቋማችን ፍንክች አለማለታችንና በጽናት መቀጠላችን ለይሖዋ ክብር ያመጣል (w08 10/15 15 አን. 16)
መዝ 83:17, 18—በጽንፈ ዓለም ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው ይሖዋ ነው (w11 5/15 16 አን. 1-2፤ w08 10/15 15-16 አን. 17-18)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
መዝ 79:9—ይህ ጥቅስ ከጸሎት ጋር በተያያዘ ምን ያስተምረናል? (w06 7/15 12 አን. 5)
መዝ 86:5—ይሖዋ ‘ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነው’ በምን መንገድ ነው? (w06 7/15 12 አን. 9)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) መዝ 85:8–86:17
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg ትምህርት 7 አን. 1
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg ትምህርት 7 አን. 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg ትምህርት 7 አን. 7-8
ክርስቲያናዊ ሕይወት
አምላክ ስም አለው?፦ (15 ደቂቃ) በjw.org ላይ የሚገኘውን “አምላክ ስም አለው?” የሚለውን ቪዲዮ በማጫወት ጀምር። (የሕትመት ውጤቶች > መጻሕፍትና ብሮሹሮች የሚለውን ክፈት። ከዚያም ከአምላክ የተላከ ምሥራች የሚለውን ክፈት። ቪዲዮው “አምላክ ማን ነው?” በሚለው ርዕስ ሥር ይገኛል።) ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስንመሠክር፣ የአደባባይ ምሥክርነት ስንሰጥ እና ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል ይህን ቪዲዮ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? ይህን ቪዲዮ ስትጠቀሙ ምን ግሩም ተሞክሮ አግኝታችኋል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) ia ምዕ. 16 አን. 1-15
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 143 እና ጸሎት
ማሳሰቢያ፦ እባክህ መጀመሪያ ሙዚቃውን ብቻ አንድ ጊዜ አጫውት፤ ከዚያ ጉባኤው አዲሱን መዝሙር አብሮ እንዲዘምር ጋብዝ።