ክርስቲያናዊ ሕይወት
ሁኔታችሁ ቢለወጥም ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሁኑ
በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ የማይቀር ነገር ነው፤ በተለይ ደግሞ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ይህ የሚጠበቅ ነው። (1ቆሮ 7:31) ያጋጠመን ለውጥ ጥሩም ሆነ መጥፎ፣ የጠበቅነውም ሆነ ያልጠበቅነው በአምልኳችንና ከይሖዋ ጋር ባለን ዝምድና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ታዲያ ለውጥ ሲያጋጥመን ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሆነን ለመኖር ምን ሊረዳን ይችላል? አካባቢ ብንቀይርም መንፈሳዊነታችንን መጠበቅ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አንድ ወንድም ለአባትየው ምን ምክር ሰጠው?
ይህ ቤተሰብ በማቴዎስ 7:25 ላይ የሚገኘው መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ ያደረገው እንዴት ነው?
ቤተሰቡ ወደ ሌላ አካባቢ ከመዛወሩ በፊት ምን ዓይነት ዕቅዶች አወጣ? ይህስ የቤተሰቡን አባላት የጠቀማቸው እንዴት ነው?
ቤተሰቡ ከጉባኤ እንዲሁም ከአገልግሎት ክልል ጋር በተያያዘ ካጋጠመው ለውጥ ጋር እንዲላመድ የረዳው ምንድን ነው?
በቅርቡ ምን ትላልቅ ለውጦች አጋጥመውኛል?
በዚህ ቪዲዮ ላይ የተመለከትኳቸውን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?