ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ከናሆም 1–ዕንባቆም 3
ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሁኑ
ባቢሎናውያን፣ ይሁዳን እንደሚያጠፏት የተነገረው ትንቢት የሚፈጸም አይመስልም ነበር። ይሁዳ፣ ኃያል ለሆነችው ግብፅ ግብር ከፍላ ስለነበር የእሷን ድጋፍ እንደምታገኝ ተማምናለች። ከለዳውያን ደግሞ ከግብፅ የበለጠ ኃይል እንደሌላቸው አይሁዳውያኑ ያስቡ ነበር። በተጨማሪም በርካታ አይሁዳውያን፣ ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሷ እንዲጠፉ ይሖዋ ፈጽሞ እንደማይፈቅድ እርግጠኞች ነበሩ። ያም ቢሆን ይሖዋ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙ የማይቀር ነበር፤ በመሆኑም ዕንባቆም ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ ሆኖ በመኖር ትንቢቱ የሚፈጸምበትን ጊዜ በተስፋ መጠባበቅ ነበረበት።
የዚህ ሥርዓት መጨረሻ በጣም እንደቀረበ እርግጠኛእንድሆን ያደረገኝ ምንድን ነው?
ምንጊዜም በመንፈሳዊ ንቁና ዝግጁ መሆን የምችለው እንዴት ነው?