ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሮም 12-14
ክርስቲያናዊ ፍቅር ማሳየት ሲባል ምን ማለት ነው?
ክርስቲያናዊ ፍቅር ካለን አንድ ሰው ሲበድለን የበቀል እርምጃ ከመውሰድ መቆጠባችን ብቻ በቂ አለመሆኑን እንገነዘባለን። መጽሐፍ ቅዱስ “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ” ይላል። (ሮም 12:20) እንዲያውም ለበደለን ሰው ደግነት ማሳየታችን ግለሰቡ በድርጊቱ እንዲጸጸት ሊያደርገው ይችላል።
ሳታስበው የበደልከው ሰው ደግነት ቢያሳይህ ምን ይሰማሃል?