ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 3-5
የመጀመሪያው ውሸት ያስከተለው አስከፊ መዘዝ
ሰይጣን ለሔዋን ውሸት ከተናገረበት ጊዜ አንስቶ የሰው ልጆችን ሲያሳስት ቆይቷል። (ራእይ 12:9) ሰይጣን የሚያስፋፋቸው የሚከተሉት ውሸቶች ሰዎች ወደ ይሖዋ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሚሆኑት እንዴት ነው?
አምላክ የለም
አምላክ ሚስጥር የሆነ ሥላሴ ነው
አምላክ ስም የለውም
አምላክ ሰዎችን በእሳታማ ሲኦል ውስጥ ለዘላለም ያሠቃያል
ሁሉም ነገር የሚከሰተው በአምላክ ፈቃድ ነው
አምላክ ለሰው ልጆች ምንም ደንታ የለውም
ሰይጣን አምላክን አስመልክቶ የሚያስፋፋቸውን እነዚህን ውሸቶች ስትሰማ ምን ይሰማሃል?
የአምላክን ስም ከነቀፋ ነፃ ለማድረግ የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችለው እንዴት ነው?