የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—ግንቦት 2020
ከግንቦት 4-10
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 36–37
“ዮሴፍ የቅናት ሰለባ ሆነ”
(ዘፍጥረት 37:3, 4) እስራኤል ዮሴፍን የወለደው በስተርጅናው ስለነበር ከሌሎቹ ወንዶች ልጆቹ ሁሉ ይበልጥ ይወደው ነበር፤ ለእሱም ልዩ የሆነ ቀሚስ አሠራለት። 4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነሱ አስበልጦ እንደሚወደው ሲያዩ ይጠሉት ጀመር፤ በሰላምም ሊያናግሩት አልቻሉም።
“ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”
መጽሐፍ ቅዱስ “ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም” በማለት መልሱን ይሰጠናል። (ዘፍጥረት 37:4) የዮሴፍ ወንድሞች የቀኑበትን ምክንያት ለመረዳት አዳጋች ባይሆንም እንደ መርዝ አደገኛ በሆነው በዚህ ስሜት መሸነፋቸው ግን ሞኝነት ነበር። (ምሳሌ 14:30፤ 27:4) አንተስ ልታገኘው የምትፈልገው ትኩረት ወይም ክብር ለሌላ ሰው በመሰጠቱ ቅናት ቢጤ የተሰማህ ጊዜ አለ? የዮሴፍን ወንድሞች አስታውስ። ያደረባቸው ቅናት የኋላ ኋላ አምርረው የተጸጸቱበትን ድርጊት ወደመፈጸም መርቷቸዋል። የእነሱ ምሳሌ፣ “ደስ ከተሰኙ ሰዎች ጋር ደስ [መሰኘት]” የጥበብ አካሄድ መሆኑን ለክርስቲያኖች ትምህርት ይሰጣቸዋል።—ሮም 12:15
ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ በጥላቻ ዓይን እንደሚመለከቱት ሳይገባው አልቀረም። ታዲያ ወንድሞቹ አጠገብ ሲሆን ያንን የሚያምር ልብሱን ደብቆት ይሆን? እንዲህ ለማድረግ ተፈትኖ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ያዕቆብ ልብሱን ለዮሴፍ የሰጠው እሱን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከተውና እንደሚወድደው ለመግለጽ እንደሆነ አስታውስ። ዮሴፍ፣ የሚተማመንበትን አባቱን ማሳፈር ስላልፈለገ ልብሱን አዘውትሮ ይለብሰው ነበር። የእሱ ምሳሌነት ለእኛም ጠቃሚ ነው። በሰማይ ያለው አባታችን ፈጽሞ የማያዳላ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮቹ ከሌሎች የተለየ ክብር ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም ከዚህ ብልሹና ሥነ ምግባር የጎደለው ዓለም የተለዩ እንዲሆኑ ይጠብቅባቸዋል። እንደ ዮሴፍ ልዩ ልብስ ሁሉ የእውነተኛ ክርስቲያኖች ምግባርም በዙሪያቸው ካሉ ሰዎች የተለዩ ያደርጋቸዋል። መልካም ምግባራቸው አንዳንድ ጊዜ ሌሎች እንዲቀኑባቸውና እንዲጠሏቸው ያደርጋል። (1 ጴጥሮስ 4:4) ታዲያ አንድ ክርስቲያን የአምላክ አገልጋይ መሆኑን መደበቅ ይኖርበታል? ዮሴፍ ልብሱን እንዳልደበቀ ሁሉ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ማንነቱን አይደብቅም።—ሉቃስ 11:33
(ዘፍጥረት 37:5-9) በኋላም ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ እነሱም እሱን የሚጠሉበት ተጨማሪ ምክንያት አገኙ። 6 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እባካችሁ ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ፣ ስሙኝ። 7 በእርሻ መካከል ነዶ እያሰርን ነበር፤ ከዚያም የእኔ ነዶ ተነስታ ቀጥ ብላ ስትቆም የእናንተ ነዶዎች ደግሞ የእኔን ነዶ ከበው ሰገዱላት።” 8 ወንድሞቹም “በእኛ ላይ ንጉሥ ልትሆንና ልትገዛን ታስባለህ ማለት ነው?” አሉት። በመሆኑም ያየው ሕልምና የተናገረው ነገር እሱን ይበልጥ እንዲጠሉት አደረጋቸው። 9 ከዚያም ሌላ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ሌላም ሕልም አለምኩ። አሁን ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና 11 ከዋክብት ሲሰግዱልኝ አየሁ።”
(ዘፍጥረት 37:11) ወንድሞቹም ይበልጥ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።
“ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”
ለዮሴፍ እንዲህ ዓይነት ሕልሞች ያሳየው ይሖዋ አምላክ ነበር። ሕልሞቹ ትንቢታዊ መልእክት ያዘሉ ሲሆኑ አምላክ ይህን መልእክት ዮሴፍ እንዲያስተላልፍ ፈልጓል። በአንድ በኩል ሲታይ ከዮሴፍ የሚጠበቀው ነገር፣ ከጊዜ በኋላ የተነሱ ነቢያት የአምላክን መልእክቶችና ፍርዶች ከሃዲ ለነበረው ሕዝቡ ሲያስተላልፉ ካደረጉት ነገር ጋር የሚመሳሰል ነው።
ዮሴፍ ወንድሞቹን “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ” በማለት በዘዴ ጠየቃቸው። ወንድሞቹ የሕልሙ ትርጉም ሲገባቸው ፈጽሞ አልተደሰቱም። “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት። ዘገባው አክሎ “ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት” ይላል። ዮሴፍ ሁለተኛውን ሕልም ለአባቱና ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የሰጡት ምላሽ ከፊተኛው ብዙም የሚሻል አልነበረም። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “አባቱ ‘ይህ ያየኸው ሕልም ምንድን ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጐንብሰን በእርግጥ ልንሰግድልህ ነው?’ ሲል ገሠጸው።” ይሁን እንጂ ያዕቆብ ጉዳዩን በልቡ ይዞ ያሰላስለው ነበር። ይሖዋ በዚህ ልጅ በኩል መልእክት እያስተላለፈ ይሆን?—ዘፍጥረት 37:6, 8, 10, 11
ዮሴፍ ሰሚዎቹን የማያስደስት አልፎ ተርፎም ስደት የሚያስከትል ትንቢታዊ መልእክት እንዲያስተላልፍ የተጠየቀ የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው የይሖዋ አገልጋይ አይደለም። እንዲህ ዓይነት መልእክት እንዲያስተላልፉ ከተላኩት ሁሉ የሚበልጠው ኢየሱስ ሲሆን ለተከታዮቹ “እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል” በማለት ነግሯቸው ነበር። (ዮሐንስ 15:20) በሁሉም ዕድሜ ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖች ወጣቱ ዮሴፍ ካሳየው እምነትና ድፍረት ብዙ ነገር መማር ይችላሉ።
(ዘፍጥረት 37:23, 24) ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰም የለበሰውን ያን ልዩ ቀሚስ ገፈፉት፤ 24 ወስደውም የውኃ ጉድጓዱ ውስጥ ጣሉት። ጉድጓዱም ባዶ ነበር፤ ውኃም አልነበረበትም።
(ዘፍጥረት 37:28) ምድያማውያን ነጋዴዎች በአጠገባቸው ሲያልፉም ዮሴፍን ከውኃ ጉድጓዱ አውጥተው በ20 የብር ሰቅል ለእስማኤላውያን ሸጡት። እነሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት
(ዘፍጥረት 36:1) የኤሳው ማለትም የኤዶም ታሪክ ይህ ነው።
it-1 678
(ኤዶም) [ቀይ]፣ ኤዶማውያን።
ኤዶም የሚለው መጠሪያ የያዕቆብ መንትያ ለሆነው ለኤሳው የተሰጠው ሁለተኛ ስም ወይም ቅጽል ስም ነበር። (ዘፍ 36:1) ኤሳው ይህ ስም የተሰጠው ለቀይ ወጥ ሲል የብኩርና መብቱን ስለሸጠ ነው። (ዘፍ 25:30-34) የሚገርመው፣ ኤሳው ሲወለድ መልኩ ቀይ ነበር (ዘፍ 25:25)፤ እሱና ዘሮቹ ከጊዜ በኋላ በኖሩበት አካባቢም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አፈሩና ድንጋዩ ቀላ ያለ ቀለም ነበረው።
(ዘፍጥረት 37:29-32) በኋላም ሮቤል ወደ ውኃ ጉድጓዱ ተመልሶ ዮሴፍ በዚያ አለመኖሩን ሲመለከት ልብሱን ቀደደ። 30 ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ “ልጁ የለም! እንግዲህ ምንድን ነው የማደርገው?” አላቸው። 31 ስለዚህ የዮሴፍን ቀሚስ ወሰዱ፤ አንድ ፍየል ካረዱ በኋላም ቀሚሱን ደሙ ውስጥ ነከሩት። 32 ከዚያም ያን ልዩ ቀሚስ እንዲህ ከሚል መልእክት ጋር ወደ አባታቸው ላኩት፦ “ይህን አገኘን፤ እባክህ ይህ የልጅህ ቀሚስ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው።”
it-1 561-562
አደራ
አንድ እረኛ አንድን መንጋ ለመጠበቅ መስማማቱ እነዚህን እንስሳት በአደራ እንደተቀበለና ሕጋዊ ኃላፊነት እንዳለበት አምኖ እንደተቀበለ የሚያሳይ ነው። ይህም እረኛው እንስሳቱን እንደሚመግባቸውና እንዳይሰረቁ እንደሚጠብቃቸው፣ እንዲህ ሳያደርግ ከቀረ ግን ካሳ እንደሚከፍል ለእንስሳቱ ባለቤት ዋስትና የሚሰጥ ነበር። ይህ ሲባል ግን እረኛው ለሁሉም ነገር ኃላፊነት ይወስዳል ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም ከላይ የተጠቀሰው ሕግ በዱር እንስሳ እንደመጠቃት ያሉ ከሰው ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እረኛውን ከተጠያቂነት ነፃ ያወጣው ነበር። ከተጠያቂነት ነፃ ለመሆን ግን እረኛው ማስረጃ ማቅረብ፣ ለምሳሌ አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ በድን ለመንጋው ባለቤት ማሳየት ይጠበቅበት ነበር። ባለቤቱም እንዲህ ያለውን ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ እረኛውን ከበደል ነፃ ሊያደርገው ይገባል።
ይኸው ሕግ በአደራ ከተሰጠ ከማንኛውም ነገር ጋር በተያያዘ ይሠራ ነበር፤ በቤተሰብ ውስጥ እንኳ የቤቱ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ለታናናሽ ወንድሞቹና እህቶቹ ጥበቃ የማድረግ ሕጋዊ ኃላፊነት ነበረበት። ከዚህ አንጻር የበኩር ልጅ የሆነው ሮቤል ዘፍጥረት 37:18-30 ላይ በተገለጸው መሠረት ወንድሞቹ ዮሴፍን ለመግደል ሲመካከሩ ሲሰማ የዮሴፍን ሕይወት የማትረፉ ጉዳይ በጣም ያሳሰበው ለምን እንደሆነ መረዳት አይከብደንም። “‘ሕይወቱን እንኳ አናጥፋ’ አለ። ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ ‘ደም አታፍስሱ። . . . ጉዳት አታድርሱበት።’ ይህን ያላቸው ከእነሱ ሊያስጥለውና ወደ አባቱ ሊመልሰው አስቦ ነበር።” ሮቤል፣ ዮሴፍ በቦታው እንደሌለ ሲያውቅ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ “ልብሱን ቀደደ።” ከዚያም “ልጁ የለም! እንግዲህ ምንድን ነው የማደርገው?” በማለት ጮኸ። ሮቤል ለዮሴፍ መጥፋት በኃላፊነት ሊጠየቅ እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር። ወንድሞቹ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ ዮሴፍ በአውሬ ተበልቶ እንደሞተ የሚያስመስል ተንኮል ሸረቡ። የዮሴፍን ልዩ ቀሚስ ወስደው የፍየል ደም ውስጥ ነከሩት። ከዚያም ጉዳዩን የመዳኘት ኃላፊነት ለነበረበት ለአባታቸው ለያዕቆብ ማስረጃ አድርገው አቀረቡለት፤ ያዕቆብም የዮሴፍ ወንድሞች ማስረጃ አድርገው ያቀረቡትን በደም የተጨማለቀውን የዮሴፍን ልብስ ሲያይ ‘ዮሴፍ በአውሬ ተገድሏል’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ ሮቤልን ከተጠያቂነት ሙሉ በሙሉ ነፃ አደረገው።—ዘፍ 37:31-33
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(ዘፍጥረት 36:1-19) የኤሳው ማለትም የኤዶም ታሪክ ይህ ነው። 2 ኤሳው ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ እነሱም የሂታዊው የኤሎን ልጅ አዳ እንዲሁም የአና ልጅና የሂዋዊው የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው ኦሆሊባማ ናቸው፤ 3 በተጨማሪም የእስማኤል ልጅ የሆነችውን የነባዮትን እህት ባሴማትን አገባ። 4 አዳ ለኤሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማት ደግሞ ረኡዔልን ወለደች፤ 5 ኦሆሊባማ የኡሽን፣ ያላምን እና ቆሬን ወለደች። እነዚህ ኤሳው በከነአን ምድር ሳለ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። 6 ከዚያም ኤሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የቤተሰቡን አባላት ሁሉ፣ መንጋውን፣ ሌሎቹን እንስሳት ሁሉና በከነአን ምድር ያፈራውን ሀብት ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ርቆ ወደ ሌላ ምድር ሄደ። 7 ምክንያቱም ንብረታቸው በጣም ስለበዛ አብረው መኖር አልቻሉም፤ እንዲሁም ከመንጋቸው ብዛት የተነሳ ይኖሩበት የነበረው ምድር ሊበቃቸው አልቻለም። 8 በመሆኑም ኤሳው በሴይር ተራራማ አካባቢ መኖር ጀመረ። ኤሳው ኤዶም ተብሎም ይጠራል። 9 በሴይር ተራራማ አካባቢ የሚኖረው የኤዶማውያን አባት የኤሳው ታሪክ ይህ ነው። 10 የኤሳው ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦ የኤሳው ሚስት የአዳ ልጅ ኤሊፋዝና የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረኡዔል ናቸው። 11 የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ቴማን፣ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም እና ቀናዝ ናቸው። 12 ቲምና የኤሳው ልጅ የኤሊፋዝ ቁባት ሆነች። ከጊዜ በኋላም ለኤሊፋዝ አማሌቅን ወለደችለት። የኤሳው ሚስት የአዳ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። 13 የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ ናቸው። እነዚህም የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ነበሩ። 14 የአና ልጅና የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለኤሳው የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ ናቸው። 15 የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሳው ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የኤሳው የበኩር ልጅ የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆችም አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ጸፎ፣ አለቃ ቀናዝ፣ 16 አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጋታም እና አለቃ አማሌቅ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሊፋዝ ልጆች ነበሩ። እነዚህ የአዳ ወንዶች ልጆች ናቸው። 17 የኤሳው ልጅ የረኡዔል ወንዶች ልጆች፣ አለቃ ናሃት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሻማህ እና አለቃ ሚዛህ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የረኡዔል ልጆች ናቸው። እነዚህ የኤሳው ሚስት የባሴማት ወንዶች ልጆች ናቸው። 18 በመጨረሻም የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ወንዶች ልጆች፣ አለቃ የኡሽ፣ አለቃ ያላም እና አለቃ ቆሬ ናቸው። እነዚህ የነገድ አለቆች የአና ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች ናቸው። 19 የኤሳው ማለትም የኤዶም ወንዶች ልጆችና አለቆቻቸው እነዚህ ናቸው።
ከግንቦት 11-17
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 38–39
“ይሖዋ ዮሴፍን ፈጽሞ አልተወውም”
(ዘፍጥረት 39:1) ዮሴፍም ወደ ግብፅ ተወሰደ፤ የፈርዖን የቤተ መንግሥት ባለሥልጣንና የዘቦች አለቃ የሆነ ጶጢፋር የሚባል አንድ ግብፃዊ ወደዚያ ይዘውት ከወረዱት እስማኤላውያን እጅ ዮሴፍን ገዛው።
‘እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት እፈጽማለሁ?’
“ዮሴፍ ወደ ግብፅ [ተወሰደ]፤ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።” (ዘፍጥረት 39:1) በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው ይህ አጭር ሐሳብ ይህ ወጣት ለሁለተኛ ጊዜ ለባርነት ሲሸጥ ሊሰማው የሚችለውን የውርደት ስሜት እንድንገምት ይረዳናል። ዮሴፍ የተቆጠረው ልክ እንደ ሸቀጥ ነው! ዮሴፍ የፈርዖን ሹም የነበረውን አዲሱን ጌታውን ተከትሎ በሕዝብ የተጨናነቁትን የከተማ ጎዳናዎች በማቋረጥ ወደ አዲሱ ቤቱ መጓዝ ጀመረ።
በመጨረሻ ቤት ደረሱ! ቤቱ ዮሴፍ ከሚያውቀው ቤት በእጅጉ የተለየ ነበር። ዮሴፍ ያደገው በግ አርቢ በሆነ ዘላን ቤተሰብ ውስጥ ነው፤ ቤተሰቦቹ የሚኖሩት በድንኳን ውስጥ ሲሆን ብዙ ጊዜ ጓዛቸውን ነቅለው ከቦታ ወደ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። እዚህ ግብፅ ውስጥ ደግሞ እንደ ጲጥፋራ ያሉ ባለጸጋ ግብፃውያን የሚኖሩት በሚያማምሩና ደማቅ ቀለም በተቀቡ ቤቶች ውስጥ ነው። የጥንቶቹ ግብፃውያን ደንገልና ሌሎች የውኃ ተክሎች የሚበቅሉባቸው ኩሬዎች እንዲሁም የጥላ ዛፎች ያሏቸው መናፈሻዎችን ይወዱ እንደነበር የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች ዘግበዋል። አንዳንዶቹ ቤቶች ዙሪያቸውን መናፈሻ ቦታ ያላቸው ሲሆን ነፋስ ለመቀበል የሚያስችል በረንዳ፣ አየር እንደ ልብ የሚያስገቡ ከፍ ብለው የተሠሩ መስኮቶች እንዲሁም ትልቅ የመመገቢያ አዳራሽና ለአገልጋዮች የተዘጋጁ ክፍሎችን ጨምሮ ብዙ ክፍሎች ያሏቸው ናቸው።
(ዘፍጥረት 39:12-14) እሷም ልብሱን አፈፍ አድርጋ ይዛ “አብረኸኝ ተኛ!” አለችው። እሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ። 13 እሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ እንደሸሸ ባየች ጊዜ 14 የቤቷን ሰዎች ጮኻ በመጣራት እንዲህ አለቻቸው፦ “አያችሁ! ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ መሳለቂያ ሊያደርገን ነው። መጥቶ አብሬሽ ካልተኛሁ አለኝ፤ እኔ ግን ጩኸቴን አቀለጥኩት።
(ዘፍጥረት 39:20) በመሆኑም የዮሴፍ ጌታ ዮሴፍን ወስዶ የንጉሡ እስረኞች የታሰሩበት እስር ቤት አስገባው፤ ዮሴፍም እዚያው እስር ቤት ውስጥ ቆየ።
‘እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት እፈጽማለሁ?’
በዚያ ዘመን ስለነበሩት የግብፃውያን እስር ቤቶች ብዙ የምናውቀው ነገር የለም። የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች የግብፃውያን እስር ቤቶችን ፍርስራሽ አግኝተዋል፤ እነዚህ እስር ቤቶች ከመሬት በታች ተቆፍረው የተሠሩ ጨለማ ክፍሎችና ሌሎች ጠባብ ክፍሎች ያሏቸው እንደ ምሽግ ያሉ ቦታዎች ነበሩ። ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ የታሰረበትን ቦታ ለመግለጽ ቃል በቃል ሲተረጎም “ጉድጓድ” የሚል ፍቺ ያለው ቃል ተጠቅሟል፤ ይህም እስር ቤቱ ብርሃን የሌለውና በቀላሉ መውጣት የማይቻልበት ስፍራ እንደሆነ ይጠቁማል። (ዘፍጥረት 40:15 NW፣ የግርጌ ማስታወሻ) በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው “እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ፤ በዐንገቱም የብረት ማነቆ ገባ” የሚለው ዘገባ ዮሴፍ ተጨማሪ ሥቃይ ደርሶበት እንደነበረ ያሳያል። (መዝሙር 105:17, 18) ግብፃውያን አንዳንድ ጊዜ የእስረኞችን እጅ በብረት የፊጥኝ ያስሩ ነበር፤ ሌሎቹን ደግሞ አንገታቸው ላይ የብረት ማነቆ ያስገቡባቸው ነበር። ዮሴፍ የደረሰበት እንግልት በጣም አሠቃይቶት መሆን አለበት፤ ይህ ሁሉ የደረሰበት ግን ምንም ጥፋት ሳይሠራ ነው።
ከዚህም በላይ ዮሴፍ እንዲህ ካለው መከራ ወዲያውኑ አልተገላገለም። ዘገባው “ዮሴፍም እዚያው እስር ቤት ውስጥ ቆየ” (NW) በማለት ይናገራል። ዮሴፍ በዚያ መጥፎ ሥፍራ ለዓመታት ቆይቷል! ደግሞም ከእስር ቤት ይውጣ አይውጣ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ዮሴፍ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ቀን ቀንን እየተካ ሳምንታት ብሎም ወራት ተቆጠሩ፤ ይሁን እንጂ ዮሴፍ ተስፋ አልቆረጠም፤ ለዚህ የረዳው ምንድን ነው?
ዘገባው ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ “ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት” ይላል። (ዘፍጥረት 39:21) የትኛውም የእስር ቤት ግድግዳ፣ ሰንሰለት ወይም ጨለማ ክፍል ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ቸርነት እንዳያሳይ ማገድ አይችልም። (ሮም 8:38, 39) ዮሴፍ በሰማይ ላለው ለሚወደው አባቱ ጭንቀቱን በጸሎት ሳይገልጽ አይቀርም፤ በመሆኑም “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ሰላምና መረጋጋት አግኝቶ መሆን አለበት። (2 ቆሮንቶስ 1:3, 4፤ ፊልጵስዩስ 4:6, 7) ይሖዋ ለዮሴፍ ሌላስ ምን ነገር አድርጎለታል? መጽሐፍ ቅዱስ “በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው” ይላል።
(ዘፍጥረት 39:21-23) ይሁን እንጂ ይሖዋ ከዮሴፍ አልተለየም፤ እንደወትሮው ሁሉ ለእሱ ታማኝ ፍቅር ከማሳየት ወደኋላ አላለም፤ በእስር ቤቱ አለቃም ፊት ሞገስ ሰጠው። 22 በመሆኑም የእስር ቤቱ አለቃ ዮሴፍን በእስር ቤቱ ውስጥ ባሉት እስረኞች ሁሉ ላይ ኃላፊ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ውስጥ እስረኞቹ የሚያከናውኑትን ማንኛውንም ሥራ የሚቆጣጠረው እሱ ነበር። 23 ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ስለነበርና የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ይሖዋ ስለሚያሳካለት የእስር ቤቱ አለቃ በዮሴፍ ኃላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ነገር ምንም አይጨነቅም ነበር።
‘እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት እፈጽማለሁ?’
ዘገባው ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ “ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት” ይላል። (ዘፍጥረት 39:21) የትኛውም የእስር ቤት ግድግዳ፣ ሰንሰለት ወይም ጨለማ ክፍል ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ቸርነት እንዳያሳይ ማገድ አይችልም። (ሮም 8:38, 39) ዮሴፍ በሰማይ ላለው ለሚወደው አባቱ ጭንቀቱን በጸሎት ሳይገልጽ አይቀርም፤ በመሆኑም “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ሰላምና መረጋጋት አግኝቶ መሆን አለበት። (2 ቆሮንቶስ 1:3, 4፤ ፊልጵስዩስ 4:6, 7) ይሖዋ ለዮሴፍ ሌላስ ምን ነገር አድርጎለታል? መጽሐፍ ቅዱስ “በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው” ይላል።
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት
(ዘፍጥረት 38:9, 10) ኦናን ግን የሚወለደው ልጅ የእሱ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር ያውቅ ነበር። በመሆኑም ለወንድሙ ዘር ላለመተካት ሲል ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር። 10 እሱም ያደረገው ነገር በይሖዋ ፊት መጥፎ ስለነበር አምላክ በሞት ቀሰፈው።
it-2 555
ኦናን
[“የማፍራት አቅም፤ የላቀ ኃይል” የሚል መሠረታዊ ትርጉም ካለው ቃል የተገኘ።]
ይሁዳ ከከነአናዊው ከሹአ ሴት ልጅ የወለደው ሁለተኛ ልጅ ነው። (ዘፍ 38:2-4፤ 1ዜና 2:3) ልጅ ያልወለደው የኦናን ታላቅ ወንድም ኤር በፈጸመው ጥፋት ምክንያት ይሖዋ ቀስፎት ከሞተ በኋላ ኦናን የኤርን ሚስት ትዕማርን አግብቶ የዋርሳነት ግዴታውን እንዲወጣ ይሁዳ ጠየቀው። ትዕማር ወንድ ልጅ ከወለደች ልጁ የኦናን ልጅ እንደሆነ ተደርጎ አይቆጠርም፤ ደግሞም ይህ ልጅ የኤር ወራሽ እንደመሆኑ መጠን ለበኩር ልጅ የሚገባውን ውርሻ የሚወስደው እሱ ይሆናል። ትዕማር ወንድ ልጅ ካልወለደች ግን ኦናን ውርሱን ለራሱ ሊወስደው ይችላል። ኦናን ከትዕማር ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ “ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር።” ኦናን በዚህ ጊዜ ማስተርቤሽን (ስሜትን ለማነሳሳትና ለማርካት ብሎ የፆታ አካልን ማሻሸት) እየፈጸመ አልነበረም፤ ምክንያቱም ዘገባው ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ የነበረው “ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ” እንደሆነ ይገልጻል። ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ ኦናን ሆን ብሎ ዘሩ ወደ ትዕማር የመራቢያ አካል ውስጥ እንዳይፈስ ያደርግ ነበር። ኦናን ስሜቱን ለማርካት ሲል ተገቢ ያልሆነ ነገር በማድረጉ ሳይሆን አባቱን ባለመታዘዙ፣ በመጎምጀቱና አምላክ ባቋቋመው የጋብቻ ዝግጅት ላይ ኃጢአት በመፈጸሙ ገና ልጅ ሳይወልድ ይሖዋ ቀስፎት ሞቷል።—ዘፍ 38:6-10፤ 46:12፤ ዘኁ 26:19
(ዘፍጥረት 38:15-18) ይሁዳም ባያት ጊዜ ዝሙት አዳሪ መሰለችው፤ ምክንያቱም ፊቷን ሸፍና ነበር። 16 ስለሆነም ከመንገዱ ወጣ በማለት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ “እባክሽ አብሬሽ እንድተኛ ፍቀጂልኝ” አላት፤ ይህን ያደረገውም ምራቱ መሆኗን ስላላወቀ ነው። ሆኖም እሷ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። 17 እሱም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እሷ ግን “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህ?” አለችው። 18 እሱም “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እሷም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም በእጅህ የያዝከውን በትርህን ስጠኝ” አለችው። ከዚያም እነዚህን ነገሮች ሰጣት፤ ከእሷም ጋር ተኛ፤ ከእሱም ፀነሰች።
የአንባቢያን ጥያቄዎች
ይሁዳ በገባው ቃል መሠረት ልጁ ሴሎም ትዕማርን እንዲያገባት አለማድረጉ ስህተት ነበር። እንዲሁም ጋለሞታ ከመሰለችው ሴት ጋር የጾታ ግንኙነት መፈጸሙ በትዳር ውስጥ ብቻ የጾታ ግንኙነት እንዲፈጸም ከሚያዘው የአምላክ ዓላማ ጋር የሚጋጭ ነው። (ዘፍጥረት 2:24) እንደ እውነቱ ከሆነ ይሁዳ የጾታ ግንኙነት የፈጸመው ከጋለሞታ ጋር አልነበረም። ከዚህ ይልቅ የወንድሙን ሚስት ማግባት ይጠበቅበት የነበረውን የልጁን የሴሎምን ቦታ ሳያውቀው የወሰደ ሲሆን የተወለደው ልጅም ሕጋዊ ወራሽ ሆኗል።
ትዕማርም ብትሆን ይህ ድርጊቷ ዝሙት ፈጽማለች ሊያስብላት አይችልም። የወለደቻቸው መንትያ ልጆችም በዝሙት የተገኙ ልጆች ተደርገው አይቆጠሩም። በቤተ ልሔም ይኖር የነበረው ቦዔዝ ለሟች ዘመዱ ወራሽ ለማስገኘት ሞዓባዊቷን ሩትን ባገባ ጊዜ የቤተ ልሔም ሽማግሌዎች “ቤትህም እግዚአብሔር ከዚህች ቆንጆ ከሚሰጥህ ዘር ትዕማር ለይሁዳ እንደ ወለደችው እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” ብለው በመመረቅ የትዕማርን ልጅ ፋሬስን በበጎ አንስተውት ነበር። (ሩት 4:12) እንዲሁም ፋሬስ በኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ ውስጥ ተጠቅሷል።—ማቴዎስ 1:1-3፤ ሉቃስ 3:23-33
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(ዘፍጥረት 38:1-19) በዚሁ ጊዜ አካባቢ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ በመውረድ ሂራ በሚባል አዱላማዊ ሰው አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ። 2 በዚያም ሹአ የሚባል የአንድ ከነአናዊ ሰው ሴት ልጅ አየ። እሷንም አገባትና ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ 3 እሷም ፀነሰች። ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤር አለው። 4 ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኦናን አለችው። 5 በድጋሚም ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም አለችው። እሱም ልጅ በወለደችለት ጊዜ አክዚብ በሚባል ቦታ ነበር። 6 ከጊዜ በኋላ ይሁዳ ለበኩር ልጁ ለኤር ሚስት አመጣለት፤ ስሟም ትዕማር ይባል ነበር። 7 ይሁንና የይሁዳ የበኩር ልጅ ኤር ይሖዋ ያዘነበት ሰው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ በሞት ቀሰፈው። 8 በዚህ የተነሳ ይሁዳ ኦናንን “ከወንድምህ ሚስት ጋር ግንኙነት በመፈጸም የዋርሳነት ግዴታህን ተወጣ፤ ለወንድምህም ዘር ተካለት” አለው። 9 ኦናን ግን የሚወለደው ልጅ የእሱ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር ያውቅ ነበር። በመሆኑም ለወንድሙ ዘር ላለመተካት ሲል ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር። 10 እሱም ያደረገው ነገር በይሖዋ ፊት መጥፎ ስለነበር አምላክ በሞት ቀሰፈው። 11 ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ ይህን ያላት ‘እሱም እንደ ወንድሞቹ ሊሞትብኝ ይችላል’ ብሎ ስላሰበ ነው። ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት መኖር ጀመረች። 12 የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላም የሹአ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳም ሐዘን ተቀምጦ ተነሳ፤ ከዚያም ከአዱላማዊው ወዳጁ ከሂራ ጋር በመሆን በጎቹን የሚሸልቱለት ሰዎች ወዳሉበት ወደ ቲምና ሄደ። 13 ትዕማርም “አማትሽ በጎቹን ለመሸለት ወደ ቲምና እየወጣ ነው” ተብሎ ተነገራት። 14 በዚህ ጊዜ የመበለትነት ልብሷን በማውለቅ የአንገት ልብስ ተከናንባና ፊቷን ተሸፍና ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው በኤናይም መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው ሴሎም ቢያድግም ለእሱ እንዳልተዳረች ስላየች ነው። 15 ይሁዳም ባያት ጊዜ ዝሙት አዳሪ መሰለችው፤ ምክንያቱም ፊቷን ሸፍና ነበር። 16 ስለሆነም ከመንገዱ ወጣ በማለት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ “እባክሽ አብሬሽ እንድተኛ ፍቀጂልኝ” አላት፤ ይህን ያደረገውም ምራቱ መሆኗን ስላላወቀ ነው። ሆኖም እሷ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። 17 እሱም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እሷ ግን “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህ?” አለችው። 18 እሱም “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እሷም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም በእጅህ የያዝከውን በትርህን ስጠኝ” አለችው። ከዚያም እነዚህን ነገሮች ሰጣት፤ ከእሷም ጋር ተኛ፤ ከእሱም ፀነሰች። 19 ከዚያ በኋላ ተነስታ ሄደች፤ የአንገት ልብሷንም አውልቃ የመበለትነት ልብሷን ለበሰች።
ከግንቦት 18-24
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 40–41
“ይሖዋ ዮሴፍን ታደገው”
(ዘፍጥረት 41:9-13) በዚህ ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ኃጢአቴን ዛሬ ልናዘዝ። 10 ፈርዖን በአገልጋዮቹ ተቆጥቶ ነበር። በመሆኑም እኔንና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ በዘቦቹ አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ውስጥ አስሮን ነበር። 11 ከዚያም ሁለታችንም በአንድ ሌሊት ሕልም አለምን። እኔም ሆንኩ እሱ ያለምነው ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። 12 ከእኛም ጋር የዘቦቹ አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ወጣት ዕብራዊ ነበር። ያየናቸውንም ሕልሞች በነገርነው ጊዜ የእያንዳንዳችንን ሕልም ፈታልን። 13 ነገሩ ሁሉ ልክ እሱ እንደፈታልን ሆነ። እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስኩ፤ ሌላኛው ሰው ግን ተሰቀለ።”
“ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”
የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን ቢረሳውም ይሖዋ ግን ፈጽሞ አልረሳውም። አንድ ቀን ይሖዋ ለፈርዖን ሁለት ሕልሞች አሳየው። በመጀመሪያው ሕልም ላይ ንጉሡ ቁመናቸው ያማረ ሰባት የሰቡ ላሞችና ከእነሱ በኋላ ደግሞ አስቀያሚ መልክ ያላቸው ከሲታ የሆኑ ሰባት ላሞች ከአባይ ወንዝ ሲወጡ ተመለከተ። ከሲታዎቹ ላሞች የሰቡትን ላሞች በሏቸው። በኋላም ፈርዖን በሕልሙ ፍሬያቸው የተንዠረገገና ያማሩ ሰባት የእህል ዛላዎች ተመለከተ። ከዚያም የቀጨጩና በነፋስ የተመቱ ሰባት የእህል ዛላዎች ወጡ፤ እነዚህ ዛላዎች ፍሬያቸው የተንዠረገጉና ያማሩ የሆኑትን የእህል ዛላዎች ዋጧቸው። ፈርዖን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ በሕልሞቹ የተነሳ እጅግ ታወከ፤ በመሆኑም የግብፅን ጠቢባንና አስማተኛ የሆኑትን ካህናት በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን እንዲተረጉሙለት ጠየቃቸው። ሆኖም ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አልነበረም። (ዘፍጥረት 41:1-8) እነዚህ ሰዎች መናገር ተስኗቸው ይሁን አለዚያም እርስ በርስ የሚጋጩ የተለያዩ ሐሳቦችን አቅርበው ሁኔታውን በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም። ያም ሆነ ይህ ፈርዖን ያሰበው ነገር አልተሳካለትም፤ በመሆኑም የሕልሞቹን ፍቺ ለማወቅ ይበልጥ ጓጓ።
በመጨረሻ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አስታወሰው! በዚህ ጊዜ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው፤ ከዚያም ከሁለት ዓመታት በፊት እሱና የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ እስር ቤት ሳሉ ሕልማቸውን በትክክል የተረጎመላቸው አንድ ወጣት እንደነበር ለፈርዖን ነገረው። ፈርዖንም ወዲያውኑ ዮሴፍን ከእስር ቤት እንዲያመጡት ሰዎች ላከ።—ዘፍጥረት 41:9-13
(ዘፍጥረት 41:16) በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን “ኧረ እኔ እዚህ ግባ የምባል ሰው አይደለሁም! ለፈርዖን መልካም የሆነውን ነገር የሚያሳውቀው አምላክ ነው” ሲል መለሰለት።
(ዘፍጥረት 41:29-32) “በመላው የግብፅ ምድር እህል እጅግ የሚትረፈረፍባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። 30 ከዚያ በኋላ ግን ረሃብ የሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። በግብፅ ምድር እህል የተትረፈረፈበት ዘመን ፈጽሞ ይረሳል፤ ረሃቡም ምድሪቱን በእጅጉ ይጎዳል። 31 ከዚያ በኋላ በሚከሰተው ረሃብ የተነሳ በምድሪቱ እህል የተትረፈረፈበት ጊዜ ፈጽሞ አይታወስም፤ ምክንያቱም ረሃቡ በጣም አስከፊ ይሆናል። 32 ሕልሙ ለፈርዖን ሁለት ጊዜ መታየቱ ነገሩ በእውነተኛው አምላክ ዘንድ የተቆረጠ መሆኑን ያሳያል፤ እውነተኛውም አምላክ ይህን በቅርቡ ይፈጽመዋል።
“ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”
ይሖዋ ትሑትና ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ይወዳል፤ ስለሆነም ከጥበበኞቹና ከካህናቱ የተሰወረውን የሕልሙን ፍቺ ለዮሴፍ መግለጡ አያስደንቅም። ዮሴፍ፣ ፈርዖን ያያቸው ሁለት ሕልሞች ተመሳሳይ ትርጉም እንዳላቸው ገለጸ። ይሖዋ፣ ነገሩ ሁለት ጊዜ እንዲታይ ማድረጉ ጉዳዩ “የተቆረጠ” መሆኑንና መፈጸሙ እንደማይቀር የሚያመለክት ነበር። የሰቡት ላሞችና ያማሩት የእህል ዛላዎች በግብፅ የተትረፈረፈ ምርት የሚኖርባቸውን ሰባት ዓመታት የሚያመለክቱ ሲሆኑ ከሲታዎቹ ላሞችና የቀጨጩት የእህል ዛላዎች ደግሞ የጥጋብ ዓመታቱን ተከትለው የሚመጡ ሰባት የረሃብ ዓመታትን የሚያመለክቱ ነበሩ። ዮሴፍ፣ ረሃቡ አገሪቱን እጅግ እንደሚጎዳት ገለጸ።—ዘፍጥረት 41:25-32
(ዘፍጥረት 41:38-40) በመሆኑም ፈርዖን አገልጋዮቹን “ታዲያ የአምላክ መንፈስ ያለበት እንዲህ ያለ ሌላ ሰው ሊገኝ ይችላል?” አላቸው። 39 ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አምላክ ይህን ሁሉ እንድታውቅ ስላደረገህ እንደ አንተ ያለ ልባምና ጠቢብ ሰው የለም። 40 አንተው ራስህ በቤቴ ላይ ትሾማለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ያላንዳች ማንገራገር ይታዘዝልሃል። እኔ ከአንተ የምበልጠው ንጉሥ በመሆኔ ብቻ ይሆናል።”
“ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”
ፈርዖን የተናገረውን ቃል የሚፈጽም ሰው ነበር። በመሆኑም ዮሴፍን ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው። በአንገቱ ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቀለት፤ የማኅተም ቀለበቱን ሰጠው፤ እንዲሁም በክብር ሠረገላው ላይ አስቀመጠው፤ ከዚያም በአገሪቱ በሙሉ በመዘዋወር ዕቅዱን እንዲያስፈጽም ሙሉ ሥልጣን ሰጠው። (ዘፍጥረት 41:42-44) እንግዲህ ዮሴፍ በአንድ ጀምበር ከወኅኒ ቤት ወጥቶ ቤተ መንግሥት ገባ። ያን ዕለት ጠዋት ተራ እስረኛ የነበረው ሰው ማታ ላይ ከፈርዖን ቀጥሎ ሁለተኛ ገዢ ሆነ። ዮሴፍ በይሖዋ መታመኑ በእርግጥም ትክክል ነበር! ይሖዋ በእነዚህ ዓመታት ሁሉ በአገልጋዩ ላይ የደረሰውን በደል ተመልክቷል። እንዲሁም በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው መንገድ ሁኔታው እንዲስተካከል አድርጓል። ይሖዋ ይህን ያደረገው ዮሴፍን ከሚደርስበት ግፍ ነፃ ለማውጣት ብቻ ሳይሆን ወደፊት የሚቋቋመውን የእስራኤል ብሔር ለመታደግ በማሰብ ነበር። ይህ የሆነው እንዴት እንደሆነ ወደፊት በዚህ ዓምድ ሥር በሚወጣ ርዕስ ላይ ይብራራል።
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት
(ዘፍጥረት 41:14) ስለሆነም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ሰዎች ላከ፤ እነሱም ከእስር ቤቱ በፍጥነት ይዘውት መጡ። እሱም ተላጭቶና ልብሱን ለውጦ ወደ ፈርዖን ገባ።
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ዮሴፍ፣ ፈርዖን ፊት ከመቅረቡ በፊት የተላጨው ለምንድን ነው?
የዘፍጥረት ዘገባ እንደሚያሳየው ፈርዖን ያስጨነቁትን ሕልሞች እንዲፈታለት በእስር ላይ የነበረው ዕብራዊው ዮሴፍ በአስቸኳይ እሱ ፊት እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላለፈ። በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እስር ቤት ከገባ በርከት ያሉ ዓመታት ተቆጥረው ነበር። የፈርዖን ትእዛዝ አስቸኳይ ቢሆንም ዮሴፍ ጊዜ ወስዶ ፀጉሩን ተላጭቷል። (ዘፍጥረት 39:20-23፤ 41:1, 14) የታሪኩ ጸሐፊ ብዙም አስፈላጊ የማይመስለውን ይህን ጉዳይ መጥቀሱ የግብፃውያንን ባሕል በደንብ እንደሚያውቅ ያሳያል።
በጥንት ዘመን ዕብራውያንን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ብሔራት ጢም የማሳደግ ልማድ ነበራቸው። በሌላ በኩል ግን “ከምሥራቅ ሕዝቦች መካከል ጢማቸውን የማያሳድጉት የጥንቶቹ ግብፃውያን ብቻ ነበሩ” በማለት በማክሊንቶክና በስትሮንግ የተዘጋጀው ሳይክሎፒዲያ ኦቭ ቢብሊካል፣ ቲኦሎጂካል ኤንድ ኤክለዚያስቲካል ሊትሬቸር ገልጿል።
ለመሆኑ የሚላጩት ጢማቸውን ብቻ ነበር? ቢብሊካል አርኪኦሎጂ ሪቪው የተባለው መጽሔት እንደገለጸው ከሆነ አንድ ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገባ ሲል እንደሚያደርገው ሁሉ ፈርዖን ፊት ከመቅረቡም በፊት የግብፃውያን ባሕል የሚጠይቀውን ልማድ እንዲያሟላ ይጠበቅበት ነበር። በዚህ ምክንያት ዮሴፍ በራሱም ሆነ በሰውነቱ ላይ ያለውን ፀጉር በሙሉ መላጨት ነበረበት።
(ዘፍጥረት 41:33) “ስለሆነም አሁን ፈርዖን ልባምና ጠቢብ የሆነ ሰው ይፈልግና በግብፅ ምድር ላይ ይሹም።”
የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናችን መልካም ምግባር እናሳይ
14 በጥንት ዘመናት የኖሩ አምላካዊ ፍርሃት ያላቸው ወላጆች፣ አክብሮት ከማሳየት ጋር በተያያዘ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ለልጆቻቸው በቤት ውስጥ ያስተምሯቸው ነበር። በዘፍጥረት 22:7 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው አብርሃምና ልጁ ይስሐቅ እርስ በርስ የተነጋገሩት አክብሮት በሚንጸባረቅበት መንገድ እንደሆነ ልብ በል። ዮሴፍም ከወላጆቹ ጥሩ ሥልጠና እንዳገኘ በግልጽ መመልከት ይቻላል። እስር ቤት በነበረበት ወቅት አብረውት የታሰሩትን ሰዎችም እንኳ ያነጋገራቸው በትሕትና ነበር። (ዘፍ. 40:8, 14) ፈርዖንን ያነጋገረበት መንገድም ሥልጣን ያለውን ሰው እንዴት ማነጋገር እንደሚገባው እንደተማረ ያሳያል።—ዘፍ. 41:16, 33, 34
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(ዘፍጥረት 40:1-23) ይህ ከሆነ በኋላ የግብፁ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፁን ንጉሥ በደሉ። 2 በመሆኑም ፈርዖን በሁለቱ ሹማምንቱ ማለትም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ 3 እሱም በዘቦች አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ይኸውም ዮሴፍ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ አደረገ። 4 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ፣ ዮሴፍ ከእነሱ ጋር እንዲሆንና እንዲረዳቸው መደበው፤ እነሱም ለተወሰነ ጊዜ ወህኒ ቤት ውስጥ ቆዩ። 5 እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩት የግብፁ ንጉሥ መጠጥ አሳላፊና ዳቦ ጋጋሪ በአንድ ሌሊት ሕልም አለሙ፤ የእያንዳንዳቸውም ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። 6 በማግስቱ ጠዋት ዮሴፍ ገብቶ ሲያያቸው ተክዘው አገኛቸው። 7 በመሆኑም በጌታው ቤት ከእሱ ጋር የታሰሩትን የፈርዖንን ሹማምንት “ምነው ዛሬ ፊታችሁ በሐዘን ጠቆረ?” ሲል ጠየቃቸው። 8 እነሱም “ሁለታችንም ሕልም አልመን ነበር፤ ሕልማችንን የሚፈታልን ሰው ግን አላገኘንም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። 9 በመሆኑም የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፦ “በሕልሜ ከፊት ለፊቴ አንድ የወይን ተክል አየሁ። 10 በወይኑም ተክል ላይ ሦስት ቀንበጦች ነበሩ፤ ተክሉም በማቆጥቆጥ ላይ እያለ አበባ አወጣ፤ በዘለላዎቹም ላይ ያሉት ፍሬዎች በሰሉ። 11 እኔም የፈርዖንን ጽዋ በእጄ ይዤ ነበር፤ የወይን ፍሬዎቹንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ውስጥ ጨመቅኳቸው። ከዚያም ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” 12 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እንዲህ አለው፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቀንበጦች ሦስት ቀናት ናቸው። 13 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል። አንተም የመጠጥ አሳላፊው በነበርክበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ። 14 ይሁንና ሁኔታዎች ሲስተካከሉልህ እኔን እንዳትረሳኝ። እባክህ ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ከዚህ እስር ቤት እንዲያስፈታኝም ስለ እኔ ለፈርዖን ንገረው። 15 በመሠረቱ እኔ ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት ተገድጄ ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት ውስጥ የጣሉኝ ያለምንም ጥፋት ነው።” 16 የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃም ዮሴፍ የተናገረው የሕልሙ ፍቺ መልካም መሆኑን ሲያይ እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔም ሕልም አይቼ ነበር፤ በሕልሜም ነጭ ዳቦዎች የያዙ ሦስት ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17 ከላይ ባለው ቅርጫት ውስጥ ለፈርዖን የሚቀርቡ የተለያዩ የተጋገሩ ምግቦች ነበሩ፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከተሸከምኩት ቅርጫት ውስጥ ይበሉ ነበር።” 18 ከዚያም ዮሴፍ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቅርጫቶች ሦስት ቀናት ናቸው። 19 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ራስህንም ቆርጦ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበላሉ።” 20 ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው። 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። 22 የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው። 23 ይሁንና የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ጨርሶም ረሳው።
ከግንቦት 25-31
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 42–43
“ዮሴፍ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ገዝቷል”
(ዘፍጥረት 42:5-7) ረሃቡ እስከ ከነአን ምድር ድረስ ተስፋፍቶ ስለነበር የእስራኤል ወንዶች ልጆች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ከሚመጡት ሰዎች ጋር አብረው መጡ። 6 በዚያን ጊዜ በምድሩ ላይ አስተዳዳሪ የነበረውና ለምድር ሕዝቦች ሁሉ እህል የሚሸጠው ዮሴፍ ነበር። በመሆኑም የዮሴፍ ወንድሞች መጥተው መሬት ላይ በመደፋት ሰገዱለት። 7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ሲያያቸው ወዲያውኑ አወቃቸው፤ እሱ ግን ማንነቱን ከእነሱ ደበቀ። በመሆኑም “የመጣችሁት ከየት ነው?” በማለት በቁጣ ተናገራቸው፤ እነሱም “እህል ለመግዛት ከከነአን ምድር ነው የመጣነው” አሉት።
“ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው?”
ዮሴፍ ግን ወንድሞቹን ወዲያውኑ አወቃቸው! እንዲያውም በፊቱ ተደፍተው ሲሰግዱለት ሲያይ በልጅነቱ ያጋጠመው ሁኔታ ወደ አእምሮው መጣ። ዘገባው ዮሴፍ “ያያቸው ሕልሞች ወዲያው ትዝ አሉት” ይላል፤ ዮሴፍ ገና ትንሽ ልጅ ሳለ ይሖዋ፣ ወንድሞቹ ልክ አሁን እያደረጉ እንዳሉት በፊቱ ተደፍተው የሚሰግዱለት ጊዜ እንደሚመጣ በሕልም አሳይቶት ነበር! (ዘፍጥረት 37:2, 5-9፤ 42:7, 9) ዮሴፍ ምን ያደርግ ይሆን? አቅፎ ይስማቸው ይሆን ወይስ ይበቀላቸው ይሆን?
“ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው?”
እኛ እንዲህ ያለ ለየት ያለ ሁኔታ ላያጋጥመን ይችላል። ሆኖም በዛሬው ጊዜ በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥም አለመግባባትና ግጭት የተለመደ ነው። እንዲህ ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ፍጽምና የጎደለው ልባችን የሚለውን ማዳመጥና በስሜት ተገፋፍተን እርምጃ መውሰድ ይቀናን ይሆናል። ይሁንና በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የተወውን ምሳሌ መከተልና አምላክ ጉዳዩን እንዴት እንድንይዘው እንደሚፈልግ ለማስተዋል መሞከር የጥበብ አካሄድ ነው። (ምሳሌ 14:12) ከቤተሰባችን አባላት ጋር ሰላም መፍጠራችን አስፈላጊ ቢሆንም ከይሖዋና ከልጁ ጋር ሰላም መፍጠራችን ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ አስታውሱ።—ማቴዎስ 10:37
(ዘፍጥረት 42:14-17) ይሁን እንጂ ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “‘እናንተ ሰላዮች ናችሁ!’ አልኳችሁ እኮ፤ 15 እንግዲህ ሰላዮች መሆን አለመሆናችሁ በዚህ ይረጋገጣል፤ በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ ትንሹ ወንድማችሁ ወደዚህ ካልመጣ በስተቀር ከዚህች ንቅንቅ አትሉም። 16 እናንተ እዚሁ ታስራችሁ እያላችሁ ከመካከላችሁ አንዱን ላኩትና ወንድማችሁን ይዞት ይምጣ። በዚህ መንገድ የተናገራችሁት ነገር እውነት መሆን አለመሆኑ ይረጋገጣል። አለዚያ ግን በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።” 17 ከዚያም ለሦስት ቀን አንድ ላይ እስር ቤት አቆያቸው።
“ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው?”
ዮሴፍ የወንድሞቹን ውስጣዊ ማንነት ለማወቅ የሚያስችሉ ፈተናዎችን በተከታታይ ማቅረብ ጀመረ። መጀመሪያ ላይ ከሌላ አገር የመጡ ሰላዮች እንደሆኑ በመግለጽ በአስተርጓሚ አማካኝነት በቁጣ አናገራቸው። እነሱም ሰላዮች እንዳልሆኑ ለማስረዳት ሲሉ ቤት የቀረ ታናሽ ወንድም እንዳላቸው የሚገልጸውን ወሳኝ መረጃ ጨምሮ በአጠቃላይ ስለ ቤተሰባቸው ሁኔታ ነገሩት። ዮሴፍ ደስታውን ለመደበቅ ሞከረ። ታናሽ ወንድሙ በእርግጥ በሕይወት አለ? አሁን ዮሴፍ ምን ማድረግ እንዳለበት አወቀ። “እንግዲህ ሰላዮች መሆን አለመሆናችሁ በዚህ ይረጋገጣል” ካላቸው በኋላ ይህን ታናሽ ወንድማቸውን ማየት እንደሚፈልግ ነገራቸው። በኋላም ከመካከላቸው አንዱ ተያዥ ሆኖ የሚቆይ ከሆነ የቀሩት ወደ ቤት ሄደው ታናሽ ወንድማቸውን ማምጣት እንደሚችሉ ገለጸላቸው።—ዘፍጥረት 42:9-20
(ዘፍጥረት 42:21, 22) ከዚያም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሁሉ እየደረሰብን ያለው በወንድማችን ላይ በፈጸምነው ግፍ የተነሳ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ተጨንቆ እንድንራራለት ሲማጸነን እኛ ግን አልሰማነውም። ይህ ሁሉ መከራ እየደረሰብን ያለው በዚህ ምክንያት ነው።” 22 በዚህ ጊዜ ሮቤል እንዲህ አላቸው፦ “‘በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብያችሁ አልነበረም? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም። ይኸው አሁን ደሙ ከእጃችን እየተፈለገ ነው።”
it-2 108 አን. 4
ዮሴፍ
የዮሴፍ ወንድሞች ያጋጠሟቸውን ሁኔታዎች ሲመለከቱ ከዓመታት በፊት ወንድማቸውን ለባርነት በመሸጣቸው አምላክ እየቀጣቸው እንዳለ አድርገው አሰቡ። አጠገባቸው የቆመው ወንድማቸው መሆኑን ሳያውቁ፣ እሱ ላይ ስለፈጸሙት በደል እዚያው ፊቱ ሆነው ይነጋገሩ ጀመር። ዮሴፍ ወንድሞቹ በጸጸት ተሞልተው ሲያወሩ ሲሰማ ስሜቱን መቆጣጠር ስላቃተው ከፊታቸው ዞር ብሎ አለቀሰ። ከዚያም ተመልሶ በመምጣት ታናሽ ወንድማቸውን ይዘው እስኪመጡ ድረስ እንደማይለቀው በመግለጽ ስምዖንን አሰረው።—ዘፍ 42:21-24
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት
(ዘፍጥረት 42:22) በዚህ ጊዜ ሮቤል እንዲህ አላቸው፦ “‘በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብያችሁ አልነበረም? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም። ይኸው አሁን ደሙ ከእጃችን እየተፈለገ ነው።”
(ዘፍጥረት 42:37) ሮቤል ግን አባቱን “ልጁን መልሼ ባላመጣልህ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው። ለእኔ በኃላፊነት ስጠኝ፤ እኔ ራሴ መልሼ አስረክብሃለሁ” አለው።
it-2 795
ሮቤል
ሮቤል አንዳንድ ጥሩ ባሕርያት ነበሩት። ለምሳሌ ዘጠኝ ወንድሞቹ ዮሴፍን ለመግደል ባሰቡ ጊዜ ሮቤል እንዲህ እንዳያደርጉ፣ ከዚህ ይልቅ ደረቅ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጥሉት ሐሳብ አቅርቦ ነበር፤ ሮቤል እንዲህ ያለው በድብቅ ተመልሶ መጥቶ ዮሴፍን ሊያድነው ስለፈለገ ነው። (ዘፍ 37:18-30) ከ20 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ እነዚሁ ወንድሞቹ በግብፅ ሳሉ ‘ሰላይ ናችሁ’ የሚል ክስ የተሰነዘረባቸው በዮሴፍ ላይ በፈጸሙት ግፍ የተነሳ እንደሆነ ሲናገሩ ሮቤል ዮሴፍን ለመግደል ባሴሩት ሴራ ከእነሱ ጋር እንዳልተባበረ ገልጾላቸዋል። (ዘፍ 42:9-14, 21, 22) በተጨማሪም ያዕቆብ ልጆቹ ወደ ግብፅ ባደረጉት ሁለተኛ ጉዞ ላይ ቢንያም አብሯቸው እንዳይሄድ በከለከለበት ጊዜ ሮቤል “[ቢንያምን] መልሼ ባላመጣልህ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው” በማለት የራሱን ልጆች እንደ መያዣ አድርጎ ሰጥቶ ነበር።—ዘፍ 42:37
(ዘፍጥረት 43:32) እነሱም ለዮሴፍ ለብቻው አቀረቡለት፤ ለእነሱም ለብቻቸው አቀረቡላቸው። እንዲሁም በቤቱ ለሚበሉት ግብፃውያን ለብቻቸው አቀረቡላቸው። ይህን ያደረጉት ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብረው ምግብ ስለማይበሉ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ለግብፃውያን አስጸያፊ ነገር ነው።
የዘፍጥረት መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች—ክፍል 2
43:32—ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር መብላትን እንደመርከስ የሚቆጥሩት ለምን ነበር? ይህ በዋነኝነት በሃይማኖታዊ ጥላቻ ወይም በዘር ኩራት ምክንያት ሊሆን ይችላል። ግብፃውያን በግ ጠባቂዎችንም እንደ ርኩስ ይመለከቱ ነበር። (ዘፍጥረት 46:34) ለምን? በግ ጠባቂዎች በግብፅ ማኅበረሰብ ውስጥ በመጨረሻው የኑሮ ደረጃ ላይ ይገኙ ስለነበር ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ለእርሻ ሊውል የሚችለው መሬት በጣም ውስን በመሆኑ ለመንጎቻቸው የግጦሽ መሬት የሚፈልጉ ሰዎች ይህን መሬት ስለሚሻሟቸው ሊሆን ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(ዘፍጥረት 42:1-20) ያዕቆብ በግብፅ እህል መኖሩን ባወቀ ጊዜ ወንዶች ልጆቹን “ለምን ዝም ብላችሁ እርስ በርስ ትተያያላችሁ?” አላቸው። 2 ከዚያም “በግብፅ እህል እንዳለ ሰምቻለሁ። በሕይወት እንድንኖር ወደዚያ ወርዳችሁ እህል ግዙልን፤ አለዚያ ማለቃችን ነው” አላቸው። 3 ስለሆነም አሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ወረዱ። 4 ሆኖም ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ቢንያምን “ምናልባት አደጋ ሊደርስበትና ሊሞትብኝ ይችላል” ብሎ ስላሰበ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር አላከውም። 5 ረሃቡ እስከ ከነአን ምድር ድረስ ተስፋፍቶ ስለነበር የእስራኤል ወንዶች ልጆች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ከሚመጡት ሰዎች ጋር አብረው መጡ። 6 በዚያን ጊዜ በምድሩ ላይ አስተዳዳሪ የነበረውና ለምድር ሕዝቦች ሁሉ እህል የሚሸጠው ዮሴፍ ነበር። በመሆኑም የዮሴፍ ወንድሞች መጥተው መሬት ላይ በመደፋት ሰገዱለት። 7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ሲያያቸው ወዲያውኑ አወቃቸው፤ እሱ ግን ማንነቱን ከእነሱ ደበቀ። በመሆኑም “የመጣችሁት ከየት ነው?” በማለት በቁጣ ተናገራቸው፤ እነሱም “እህል ለመግዛት ከከነአን ምድር ነው የመጣነው” አሉት። 8 ዮሴፍ ወንድሞቹን ያወቃቸው ቢሆንም እነሱ ግን አላወቁትም። 9 ዮሴፍም ስለ እነሱ ያያቸው ሕልሞች ወዲያው ትዝ አሉት፤ እሱም “እናንተ ሰላዮች ናችሁ! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች ለማየት ነው!” አላቸው። 10 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ኧረ እንደዚያ አይደለም ጌታዬ፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነው። 11 ሁላችንም የአንድ ሰው ልጆች ነን። እኛ ንጹሐን ሰዎች ነን። አገልጋዮችህ ሰላዮች አይደለንም።” 12 እሱ ግን “በፍጹም አይደለም! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች ለማየት ነው!” አላቸው። 13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ 12 ወንድማማቾች ነን። በከነአን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ ትንሹ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ነው፤ አንደኛው ግን የለም።” 14 ይሁን እንጂ ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “‘እናንተ ሰላዮች ናችሁ!’ አልኳችሁ እኮ፤ 15 እንግዲህ ሰላዮች መሆን አለመሆናችሁ በዚህ ይረጋገጣል፤ በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ ትንሹ ወንድማችሁ ወደዚህ ካልመጣ በስተቀር ከዚህች ንቅንቅ አትሉም። 16 እናንተ እዚሁ ታስራችሁ እያላችሁ ከመካከላችሁ አንዱን ላኩትና ወንድማችሁን ይዞት ይምጣ። በዚህ መንገድ የተናገራችሁት ነገር እውነት መሆን አለመሆኑ ይረጋገጣል። አለዚያ ግን በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።” 17 ከዚያም ለሦስት ቀን አንድ ላይ እስር ቤት አቆያቸው። 18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አምላክን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ። 19 እንዳላችሁት ንጹሐን ሰዎች ከሆናችሁ ከመካከላችሁ አንዱ ወንድማችሁ እዚሁ እስር ቤት ውስጥ ይቆይ፤ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ መሄድ ትችላላችሁ። 20 የተናገራችሁት ቃል እውነት መሆኑ እንዲረጋገጥና ከሞት እንድትተርፉ ትንሹን ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁት ኑ።” እነሱም እንደተባሉት አደረጉ።