የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 172
  • መግደላዊቷ ማርያም ማን ነበረች?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መግደላዊቷ ማርያም ማን ነበረች?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መግደላዊቷ ማርያም ዝሙት አዳሪ ነበረች?
  • መግደላዊቷ ማርያም “ለሐዋርያት ሐዋርያ” ነበረች?
  • መግደላዊቷ ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ሚስት ነበረች?
  • “ጌታን አየሁት!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 172
መግደላዊቷ ማርያም ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ፣ ባዶ በሆነ መቃብር ፊት ለፊት ኢየሱስን ስታገኘው።

መግደላዊቷ ማርያም ማን ነበረች?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መግደላዊቷ ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ነበረች። መግደላዊቷ የሚለው ስም የመጣው በገሊላ ባሕር አቅራቢያ ከሚገኘው የመጌዶል (መጌዶን ሊሆንም ይችላል) ከተማ ሳይሆን አይቀርም። ምናልባትም ማርያም በሆነ ወቅት ላይ ትኖር የነበረው በዚያ ከተማ ሊሆን ይችላል።

መግደላዊቷ ማርያም ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በመጓዝ ቁሳዊ ድጋፍ ይሰጧቸው ከነበሩት በርካታ ሴቶች አንዷ ነበረች። (ሉቃስ 8:1-3) በተጨማሪም ኢየሱስ ሲገደል የዓይን ምሥክር ነበረች፤ እንዲሁም ትንሣኤ ካገኘ በኋላ መጀመሪያ ላይ ከተመለከቱት ሰዎች አንዷ እሷ ነች።—ማርቆስ 15:40፤ ዮሐንስ 20:11-18

  • መግደላዊቷ ማርያም ዝሙት አዳሪ ነበረች?

  • መግደላዊቷ ማርያም “ለሐዋርያት ሐዋርያ” ነበረች?

  • መግደላዊቷ ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ሚስት ነበረች?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንት ማርያሞች ተጠቅሰዋል?

መግደላዊቷ ማርያም ዝሙት አዳሪ ነበረች?

መጽሐፍ ቅዱስ መግደላዊቷ ማርያም ዝሙት አዳሪ እንደነበረች አይገልጽም። ከዚህ ይልቅ ስለ እሷ የቀድሞ ታሪክ የሚናገረው፣ ኢየሱስ ሰባት አጋንንት እንዳስወጣላት ብቻ ነው።—ሉቃስ 8:2

ታዲያ ዝሙት አዳሪ እንደነበረች የሚገልጸው ሐሳብ የመጣው ከየት ነው? መግደላዊቷ ማርያም ከሞተች ከበርካታ መቶ ዓመታት በኋላ አንዳንድ ሰዎች የኢየሱስን እግር በእንባዋ በማራስ በፀጉሯ ያበሰችው ስሟ ያልተጠቀሰች ሴት (ይህች ሴት ዝሙት አዳሪ ሳትሆን አትቀርም) መግደላዊቷ ማርያም እንደሆነች መናገር ጀመሩ። ሆኖም እንዲህ ብሎ ለማመን የሚያበቃ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የለም።

መግደላዊቷ ማርያም “ለሐዋርያት ሐዋርያ” ነበረች?

አልነበረችም። የኢየሱስን ትንሣኤ ለሐዋርያቱ መጀመሪያ ላይ ካበሰሩት ሴቶች አንዷ መግደላዊቷ ማርያም በመሆኗ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን “ቅድስት መግደላዊቷ ማርያም” እንዲሁም “ለሐዋርያት ሐዋርያ” በማለት ትጠራታለች። (ዮሐንስ 20:18) ሆኖም የኢየሱስን ትንሣኤ ለሐዋርያት ማብሰሯ ሐዋርያ አያደርጋትም። መጽሐፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ላይ መግደላዊቷ ማርያምን “ሐዋርያ” በማለት አይጠራትም።—ሉቃስ 6:12-16

መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ የተጠናቀቀው በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ነው። ሆኖም የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመግደላዊቷ ማርያም ከፍ ያለ ቦታ መስጠት የጀመሩት በስድስተኛው ክፍለ ዘመን ነው። በሁለተኛውና በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ የተጻፉ ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያልሆኑ መጻሕፍት፣ አንዳንዶቹ የኢየሱስ ሐዋርያት በማርያም ይቀኑ እንደነበረ ይገልጻሉ። እንዲህ ያሉት የፈጠራ ታሪኮች ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም።

መግደላዊቷ ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ሚስት ነበረች?

በፍጹም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ትዳር እንዳልመሠረተ በግልጽ ያስተምራል።a

a “ኢየሱስ ትዳር መሥርቶ ነበር? ኢየሱስ ወንድሞችና እህቶች ነበሩት?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንት ማርያሞች ተጠቅሰዋል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም በሚለው ስም የተጠሩ ስድስት ሴቶች ተጠቅሰዋል።b

  1. 1. የኢየሱስ እናት።—ማቴዎስ 1:18

  2. 2. የማርታና የአልዓዛር እህት።—ዮሐንስ 11:1, 2

  3. 3. መግደላዊቷ ማርያም።—ሉቃስ 8:2

  4. 4. የያዕቆብና የዮሳ እናት።—ማቴዎስ 27:56

  5. 5. የዮሐንስ ማርቆስ እናት።—የሐዋርያት ሥራ 12:12

  6. 6. ለጉባኤው ስትል ብዙ የደከመች በሮም የምትኖር ክርስቲያን።—ሮም 16:6

b ማርያም የሚለው ስም፣ ሚርያም የተባለው የዕብራይስጥ ስም የግሪክኛ አጠራር ነው፤ ሚርያም የሙሴ እህት ነበረች።—1 ዜና መዋዕል 6:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ