የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 171
  • የዲያብሎስ መልክ ምን ዓይነት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዲያብሎስ መልክ ምን ዓይነት ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን የሚገልጸው እንዴት ነው?
  • ሰይጣንን ተቃወሙት፣ ከእናንተም ይሸሻል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ኢየሱስ እንዳደረገው “ዲያብሎስን ተቃወሙት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የዘላለም ሕይወት ጠላት
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 171

የዲያብሎስ መልክ ምን ዓይነት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ዲያብሎስ መንፈሳዊ ፍጡር ነው፤ ስለዚህ በዓይን ሊታይ የሚችል አካል የለውም።—ኤፌሶን 6:11, 12

ዲያብሎስ መንሽ ይዞ የሚያሳይ በስፋት የሚታወቅ ሥዕል። በዚህ ሥዕል ላይ ዲያብሎስ ቀንድና ጅራት ያለው ፍየል መሰል ፍጡር ተደርጎ ተሥሏል።

ብዙ ሠዓሊዎች ዲያብሎስን ቀንድና ጅራት ያለው እንዲሁም በእጁ መንሽ የያዘ ፍየል መሰል ፍጡር አድርገው ይሥሉታል። ዲያብሎስን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አስመስለው የሣሉት በመካከለኛው መቶ ዘመን የኖሩ ሠዓሊዎች እንደሆኑ አንዳንዶች ያምናሉ፤ በእነዚህ ሠዓሊዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት ደግሞ የጥንት አፈ ታሪኮች እንደሆኑ ይገመታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን የሚገልጸው እንዴት ነው?

  • ስለ ዲያብሎስ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን የሚገልጸው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዲያብሎስ ሲናገር የተለያዩ አገላለጾችን ይጠቀማል። እነዚህ አገላለጾች የዲያብሎስን መልክ ሳይሆን ማንነቱን ለማወቅ ይረዱናል። ከእነዚህ አገላለጾች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦

  • የብርሃን መልአክ። ሰዎችን የሚጠቅም መልካም ነገር እንዳለው ለማስመሰል ይሞክራል፤ ይህን የሚያደርገው ሰዎች የአምላክን ሳይሆን የእሱን ትምህርቶች እንዲከተሉ ለማድረግ ነው።—2 ቆሮንቶስ 11:14

  • የሚያገሳ አንበሳ። በአምላክ አገልጋዮች ላይ ከባድ ጥቃት ይሰነዝራል።—1 ጴጥሮስ 5:8

  • ታላቅ ዘንዶ። አስፈሪ፣ ኃይለኛና አጥፊ ነው።—ራእይ 12:9

ስለ ዲያብሎስ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

  • 2 ቆሮንቶስ 11:14፦ “ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል።”

    ትርጉሙ፦ ሰይጣን ጥሩ መስሎ ለመቅረብ ይሞክራል፤ ይህን የሚያደርገው ሰዎች የአምላክን ሳይሆን የእሱን ትምህርቶች እንዲከተሉ ለማድረግ ሲል ነው።

  • ኤፌሶን 6:11፦ “የዲያብሎስን መሠሪ ዘዴዎች መቋቋም እንድትችሉ ከአምላክ የሚገኘውን ሙሉ የጦር ትጥቅ ልበሱ።”

    ትርጉሙ፦ ዲያብሎስ ሰዎች የአምላክን ትእዛዝ እንዲጥሱ ለማድረግ ሲል የተንኮል ዘዴዎችን ይጠቀማል።

  • ያዕቆብ 4:7፦ “ራሳችሁን ለአምላክ አስገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤ እሱም ከእናንተ ይሸሻል።”

    ትርጉሙ፦ አንድ ሰው ዲያብሎስን ሳይሆን አምላክን በመታዘዝ ሰይጣንን ድል ማድረግ ይችላል።

  • 1 ጴጥሮስ 5:8፦ “ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል።”

    ትርጉሙ፦ ዲያብሎስ አምላክን የሚታዘዙ ሰዎችን ይጠላል፤ በመሆኑም ከአምላክ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ማበላሸት ይፈልጋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ